ሐምሌ 21 2017 - ''ለአፍሪካ የግብርና ዘርፍ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እንደ ጋራ ኢንቨስትመንት እንጂ እንደ እርዳታ መታየት የለበትም'' ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ
- sheger1021fm
- Jul 28
- 1 min read
ለአፍሪካ የግብርና ዘርፍ የሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ እንደ ጋራ ኢንቨስትመንት እንጂ እንደ እርዳታ መታየት የለበትም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርአት ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ ለማሳደግ ከቴክኖሎጂ እስከ ፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቅስዋል።
ድጋፉ በዕርዳታ መልክ ሳይሆን በጋራ ኢንቨስትመንት መንፈስ የሚሰጥ ሊሆን ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ከውጭ ጥገኝነት ለመላቀቅ በምርት ዕድገት ላይ እየሰራች ነውም ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በበኩላቸው የምግብ ስርአት ችግር በአለም ዙሪያ እያስከተለ ያለው ተጽዕኖ በአመት ከ10 ትሪሊየን ዶላር በላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ያለውን ሁለተኛውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርአት ጉባኤ ኢትዮጵያና ጣሊያን በትብብር አዘጋጅተውታል።
ሙሉበ ዘገባውን ያድምጡ……
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s








