top of page

ሐምሌ 19 2017 - የጎንደሯ ነዋሪ የሽቱ ምስጋናው በኢትዮጵያ ሎተሪ ታሪክ ከፍተኛ የሆነውን 50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ አሸናፊ ሆነች

  • sheger1021fm
  • Jul 26
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የሚሊዮን ሎተሪ እና የቶምቦላ እጣ ባለዕድለኞችን በዛሬው እለት ሸልሟል።


ብሔራዊ ሎተሪ ያዘጋጀው የ50 ሚሊዮ ብር ሎተሪ እጣ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም መውጣቱ ይታወሳል፡፡


በተመሳሳይ የቤት እና የመኪና ዕጣዎችም ከተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት ጋር ያቀረበው ቶምቦላ ሎተሪ ባለፈው ሰኔ 29 አሸናፊዎቹ ይፋ ማድርጉ ይታወቃል፡፡

ree

በዚህም የ50 ሚሊዮን ሎተሪ እና የቶምቦላ ሎተሪ አሸናፊወች ሽልማታቸውን ዛሬ ተረክበዋል፡፡


የሚሊዮን ሎተሪ ዕድለኞች የአንደኛ እጣ አሸናፊ የሆነችው የሽቱ ምስጋናው ከጎንደር 50 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ሆናለች፣ ሽልማቷንም ተቀብላለች።


ካሳ አለሙ አባይ የተባሉ ከትግራይ ነዋሪ ደግሞ 25 ሚሊዮን አሸናፊ ሆነዋል፣ ሽልማታቸውንም ተቀብለዋል።


በሌላ በኩል ደግሞ በቶምቦላ ሎተሪ ነጋልኝ አበራ ብሩ ከኦሮሚያ ም/ሸዋ 1ኛ ዕጣ ባለ 3 መኝታ መኖሪያ ቤት ከተጨማሪ ለ3 ዓመት 60ሺህ አሸናፊ ሆነዋል።


ሌሎችም አሸናፊዎች ሽልማቶቻቸውን ዛሬ ተቀብለዋል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page