top of page

ሐምሌ 18 2017 - "ወደ ማዶ" የተባለ ቴአትር በ30 መድረኮች ሊመደረክ ነው

  • sheger1021fm
  • Jul 25
  • 1 min read

"ወደ ማዶ" የተባለ ቴአትር በአፍሪካ፣ በአውሮፓና በአሜሪካ ያሉ ሀገሮችን ጨምሮ በ30 መድረኮች ሊመደረክ ነው፡፡


ይህ ሲሆንም በኢትዮጵያ የቴአትር ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል ሲሉ የቴአትሩ አዘጋጆችና ፕሮዲውሰሮች ተናግረዋል፡፡


ቴአትሩን በ30 የአለም ሀገራት መድረኮች ለማሳየት በቅርቡ ጉዞው ከአፍሪካ ሀገሮች ይጀመራል ሲባል ሰምተናል፡፡


በአዲስ አበባ በህዳር ወር እንደሚመረቅ ተነግሯል፡፡


ቴአትሩን ፕሮዲውስ ያደረገውና በየሀገራቱ የሚያሳየው ዋካ ፕሮሞሽንና ኢቨንት ሲሆን አዘጋጁ ደግሞ ሴማ አመኑኤል መሆኑን ሰምተናል፡፡


#ወደ_ማዶ የተሰኘውና ኮሜዲ ዘውግ ያለውን ቴአትር የደረሰው ደረሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ነው፡፡


በቴአትሩ ላይ ሃረገወይን አሰፋ፣ ሸዋፈራው ደሳለኝ እና የኋላእሸት ዘሪሁን ይተውኑበታል፡፡


ቴአያትሩ ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያነሳ፣ በሕይወት የሚገጥሙን ችግሮች ለማውጣት የሚደረግን ትንቅንቅ የሚያሳይ መሆኑን ደራሲው አስረድቷል፡፡

‘’ወደ ማዶ" አለም አቀፍ የቴአያትር ጉዞ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሚገኙባቸው በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ አህጉራት በሚገኙ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ30 በላይ መድረኮች እንደሚታይ ተነግሯል፡፡


በተጨማሪም ቴአትሩ በሚታይባቸው ሀገራትና መድረኮች ከቴአትሩ ጎን ለጎን ለ'’የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል" የገቢ ማሰባሰቢያ ይካሄዳል፡፡ ይህንንም ለማሳካት ከማዕከሉ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡


ቴአትሩን በ30 ሀገራት አሳያለሁ ያለው ዋካ ፕሮሞሽንና ኢቨንት ከዚህ ቀደም በናይጄርያ አቡጃ እና በጣሊያን (ሮም) ከተሞች የስዕል አውደ ርዕይ ከሙዚቃ ጋር የቀረበበትን ዝግጅት አካሂዷል፤ በፈረንጆቹ 2023 ደግሞ አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ግሎባል ትሬድ ኔትወርክ ጋር በጋራ በመሆን በቤልቪው ሆቴል ትሬድ ሰሚት አዘጋጅቷል ተብሏል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page