ሐምሌ 17 2017 - ብርሃንን የመለየት ችግርን ለማስተካከል ያለመ የዓይን ቀዶ ህክምና ማዕከል በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ
- sheger1021fm
- Jul 24
- 1 min read
በኢትዮጵያ የአይን ህክምና ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ብርሃንን የመለየት ችግርን ለማስተካከል ያለመ የዓይን ቀዶ ህክምና ( #Refractive_Surgery ) ማዕከል ስራ ጀመረ።
ማዕከሉን የከፈተው ብሩህ ቪዥን ልዩ የአይን ህክምና ማዕከል ነው፡፡
ሪፍራክቲቭ ሰርጀሪ የተሰኘው ይህ የዓይን ሕክምና ከሩቅና ከቅርብ ማየት አለመቻልን እንዲሁም መሰል የዕይታ ችግሮችን ለማስተካከል ያለመ የዓይን ቀዶ ህክምና ዓይነት መሆን ሲነገር ሰምተናል፡፡
በኢትዮጵያ የዓይን ህክምና የሚሰጡ የህክምና ተቋማት ጥቂት በመሆናቸው ታክመው ሊድኑ የሚችሉ የአይን ህመሞች በጊዜ መታከም እየቻሉ እንዳልሆነ የተነገረ ሲሆን ትናንት ስራውን የጀመረው ሪፍራክቲቭ ሰርጀሪ ማዕከል ያለው ችግር ያቃልላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

ቀዶ ህክምናው ከ8 እስከ 10 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚከወነው የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ለዚህ ህክምና ወደ በውጭ ሀገራት የሚደረግን የህክምና ጉዞ ያስቀራል ተብሏል።
በኢትዮጵያ የአይን ህክምና ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ብርሃንን የመለየት ችግርን ለማስተካከል ያለመ የዓይን ቀዶ ጥገና ማዕከል (ሪፍራክቲቭ ሰርጀሪ ማእከል) አገልግሎቱን ወሎ ሠፈር ቢራ ሕንጻ በሚገኘው ብሩህ ቪዥን ልዩ የአይን ህክምና ማዕከል እንደሚሠጥ ተነግሯል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s








