ሐምሌ 17 2017 - በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የመሬት መንሸራተት ቤቶችን እያፈራረሰ፣ ሰዎችን እያፈናቀለ መሆኑ ተሰማ
- sheger1021fm
- Jul 24
- 1 min read
በደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል የመሬት መንሸራተት ቤቶችን እያፈራረሰ፣ ሰዎችን እያፈናቀለ መሆኑ ተሰማ፡፡
ከፋ፣ ቤንች ሸኮ ችግሩ ከደረሰባቸው የክልሉ ዞኖች መካከል ሲሆኑ የመሬት መንሸራተት ስጋት ያለባቸው ሌሎች አካባቢዎችም አሉ ተብሏል፡፡
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ20 ቀበሌዎች ላይ የመሬት መንሸራተት አደጋ መድረሱ ተነገረ፡፡
በክልሉ 80 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው በ23.7 ሄክታር መሬት ላይ ያለሰብል ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡
በሌሎች 30 ወረዳዎች ላይም ስጋት መሆኑንና በዚህም 49 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ከክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰምተናል፡፡

ከፋ፣ ቤንች ሸኮ ችግሩ ከደረሰባቸው የክልሉ ዞኖች መካከል ናቸው፡፡ የቤት እንስሳትም ሞተዋል ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ ከ200 በላይ ሰዎች በጉዳትና በስጋት ከአካባቢያቸው እንዲወጡ መደረጉን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ለማ መለሰ ነግረውን፡፡
አሁን ላይ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉትን በመለየት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ደግሞ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን ከኮሚሽኑ ሰምተናል፡፡
አሁንም የዝናቡ ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ተብሏል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments