top of page

ሐምሌ 17 2016 - ሂጅራ ባንክ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ሲያካሂደው የነበረው ''ሲራራ አዋርድ'' የሽልማት መርሃ ግብር መጠናቀቁን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jul 25
  • 1 min read
ree

የሽልማት ስነ ስርዓቱም በዛሬው ዕለት የመንግስት ሀላፊዎች፣ የባንኩ ሀላፊዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች በተገኙበት መካሄዱ ተሰምቷል።


በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡትም መሸለማቸውን ባንኩ የላከልን መግለጫ ያስረዳልዕ።


በአንደኛ ደረጃ  ያጠናቀቀው ስራ ፈጣሪ  ሚልኪያስ አህመድ(ዶ/ር ) ሲሆን ለአሸናፊነት ያበቃውም የአፈር ማዳበሪያ ከእንስሳት አጥንት ማግኘት በመቻሉ መሆኑ ተጠቅሷል።


በዚህ የስራ ፈጠራውም የ 3,000,000 የቀርደል ሀሰን ፋይናንስኪንግዕ (ከወለድ ነፃ ብድር) እና 300,000  ብር ተሸላሚ ሆኗል።


የሂጅራ ባንክ የሲራራ ስራ ፈጠራ ውድድርን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው  ስራ ፈጣሪ  ደግሞ ዩሱፍ አሊ  ይባላል።


የፈጠረው ስራም የገበሬዎችን የዕለት ተዕለት አድካሚና ኋላቀር የአሰራር ዘዴዎችን ወደ ተሻሻለ ደረጃ ለማምጣት የሚያስችል የእህል ማጨጃ ማሽንን መሆኑን ሰምተናል።


ወጣቱ ለዚህ ፈጠራው የ1,000,000  ቀርደል ሀሰን ፋይናንሲንግ እና የ 200,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል።


እንዲሁም ሙሃመድ ጁሃር በትንሽ ኃይል የሚሰራ የዶሮ እንቁላል ማፈልፈያ ማሽን በመስራት የሶስተኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ያጠናቀቀ ሲሆን 500,000 የቀርድ ፋይናንሲንግ ሺልማት እና 100,000  ተሸላሚ መሆኑን ባንኩ ነግሮናል።


በተጨማሪም ጣሂር ኢሳ እና ኢሳቅ ጋሊ እንዲሁም ኢብራሂም አሊ በቅደም ተከተል 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page