top of page

ሐምሌ 16 2017 - የኢትዮጵያ ቅርሶች ከሀገር ሲወጡ ባለቤታቸው ስለሚቀየር ለማስመለስ አስቸጋሪ አንደሆነ ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • Jul 23
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ሥልጣኔዋን የሚያስረዱላት፣ ታሪኳን የሚናገሩለት ጥንታዊ ቅርሶቿ መላና ብልሃት እየተበጀላቸው እንዲሁም በወረራ ተወስደው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይገኛሉ፡፡


ቅርሶቹን ለማስመለስ ጥረት ሲደረግ ቢታይም አሁንም ግን ማስመለስ ከተቻለው በላይ የኢትዮጵያ ቅርሶች በየሀገሩ ሙዚየሞች እንደሚገኙ ይነገራል፡፡


ቅርሶቹን ከሀገር ሲወጡ ባለቤታቸው ስለሚቀየር ለማስመለስ አስቸጋሪ አንደሆነ ተነግሯል፡፡


በተለይም ቅርሶች ከሀገር የወጡበት ጊዜ መራቅና፣ ከሀገራት ጋር የተደረጉ የተለያዩ ስምምነቶች በጦርነት ሰበብ፣ በጉብኝትና በሌሎች ምክንቶች ከሀገር ከወጡ ከዓመታት በኋላ መሆኑ ችግሩን አክፍቶታል ተብሏል፡፡


ቅርሶች ተዘረፈዉ የሚገኙባቸዉ ሀገሮች ፖሊሲ መለያየት ሌላኛዉ ችግሩን ያከበደዉ ምክንያት ነዉ ተብሏል፡፡


እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረግሁት ከፍተኛ ጥረትና በግለሰቦች መልካም ትብብር በ2017 ዓ.ም በህገወጥ መንገድ ከሀገር የወጡ ሶስት ቅርሶችን ማስመለስ እንደቻለ ተናግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ገዛ ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page