top of page

ሐምሌ 12 2017 - ''ኪን ኢትዮጵያ'' የተባለ የኪነ ጥበብ ጉዞ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ሊዘዋወር ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jul 19
  • 1 min read

70 አባላት ያሉት የኪነ-ጥበብ ቡድን የኢትዮጵያ ቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት አማራጭና ሌሎች ሀብቶቿን ለማስተዋወቅ በማሰብ ''ኪን ኢትዮጵያ'' የተባለ የኪነ ጥበብ ጉዞ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ሊዘዋወር ነው ተባለ፡፡


ጉዞው ሐምሌ 13 የሚጀምር ሲሆን ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን በዚህ የኪነ ጥበብ ጉዞ ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል።


ጉዞውን በበላይነት ያሰናዱት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ሻኩራ ስቱዲዮ በጋራ በመሆን ነው ሲሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁ ጎበዛይ ተናግረዋል።


መንግስት ቅድሚያ በመዳረሻ ሀገራት ላይ አስፈላጊው ግንኙነትና ዝግጅቶች አድርጓል ሲሉም አክለዋል።

ree

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ከ39 ዓመት በፊት ህዝብ ለህዝብ በሚል በተመሳሳይ መንገድ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ጉዞ በተለያዩ ሃገራት አድርገው የነበረ አሁን የሚደረገው ጉዞ የኢትዮጵያ መንግስት ከመዳረሻ ሃገራት መንግስታት ጋር ቅድሚያ በጉዳዩ ላይ ኦፊሴሊያዊ ግንኙነት ማድረጉን ተናግረዋል።


ባለሙያዎቹ ኢትዮጵያ በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ያላትን ሀብት በሚገባ ያስተዋውቃሉ ሲሉም ጠቅሰዋል።


ኪን ኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ጉዞ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ያላትን ሃብት መንገርና ሃገሪቱ ያላት የኢንቨስትመንት አማራጭ ለአለም ሃገራት ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተብሏል።


አርቲስት ካሙዙ ካሳ የኪነ ጥበብ ጉዞው የመጀመሪያው የፊታችን እሁድ ወደ ቻይና በማምራት ነው ያለ ሲሆን በቻይና በሁለት ከተሞች ስራዎቹን ያቀርባል ብሏል።


ባለፉት 3 ወራት የኪነ-ጥበብ ቡድኑ ልምምድን ሲያደርግ ነበር ከሙዚቃ ስራ ባለፈም የፋሽን ትርኢትና ሌሎች ስራዎች ይቀርባሉ ሲል ተናግሯል።


የቻይናው ጉዞ ሲጠናቀቅ ቀጣይ ሃገራት ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page