ለረዥም ዓመታት ተቋርጦ የቆየዉ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዉድድር በጅማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል
- sheger1021fm
- 5 minutes ago
- 1 min read
ጥር 18/2018
ለረዥም ዓመታት ተቋርጦ የቆየዉ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዉድድር በጅማ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል::
በዉድድሩ ለመሳተፍ 49 ዩኒቨርሲቲዎች ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተዋል::
15 የተለያዩ እስፖርታዊ ዉድድሮች ይደረጋሉ ተብሏል::
በዚህ ዉድድር ከ4ሺ አምስት መቶ በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል::
ዉድድሩ ከጥር 17 እስከ የካቲት1 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚደረግም ሰምተናል::
ውድድሩ ከ2017 በነበሩት 10 አመታት ተቋርጦ የቆየ ሲሆነ አምና በመለስተኛ ተሳታፊ ዩኒቨርሲቲዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት መካሄዱ ይታወሳል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ ይህ ዉድድር ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ዉድድሮች ለየት ያለነዉ ሲሉ ተናግረዋል::

በዚህም በዘርፍ ተደጋጋሚ ጥያቄ የነበረው የስፖርት ፖሊሲ መከለስ እና ስፖርትን በህግና ስርዓት ለመምራት የሚያስችል የስፖርት ልማት አዋጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተወያየበት በኃላ ፖሊሲው እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመራበት በመሆኑ የዘንድሮን የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ስፖርት ፈስቲቫልን ልዩ ከሚያደርጉት መካከል አንዱ እንደሆነ አስረድተዋል ፡፡
ጅማ ዩኒቨርስቲ ውድድሩን ለማስተናገድ የመወዳደሪ ስፍራዎችን ከማሰናዳት ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን እንዲሁም አሁን ላይ ሁሉም ተወዳዳሪዎች ቦታ ቦታዎችን እንደያዙ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ይህ ውድድር ተቋማቱ ከእስፖርቱ በተጨማሪ የእርስ በእርስ ግኑኝነታቸውን የሚያጠናክሩበት እንዲሁም የባህል ልውውጥ የሚያደርጉበት መሆኑን ሰምተናል።
ዉድድሩ እንደሃገርም ቢሆን ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት አስተዋፆ የጎላ ነዉ ያሉት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ስፖርት ማህበር ፕሬዝደንት አባይ በላይሁን ናቸዉ::
በአጠቃላይ ይህንን ዉድድር ለማሰናዳት ከመቶ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) ተናግረዋል::
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…..
YouTube : https://url-shortener.me/2DTR
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://url-shortener.me/2DTY
WhatsApp :https://url-shortener.me/2DU0
Website፡ https://www.shegerfm.com/
LinkedIn :https://url-shortener.me/2DU8
Tiktok : https://url-shortener.me/2DUB
Instagram : https://url-shortener.me/2DUD








