top of page

ህዳር 26፣2016 - የኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉ ሃሳቦችን የማጎልበት አላማ አለው የተባለ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ

በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ላይ ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉ የመፍትሔ ሃሳቦችን የማጎልበት አላማ አለው የተባለ መርሃ ግብር ዛሬ በሸራተን አዲስ ይፋ ሆነ።


መርሃ ግብሩ በተለይም በስራ ፈጣሪዎች ላይ ላሉ የገንዘብና የባለሞያ እጥረት ችግሮች መፍትሄ ይዟል ተብሏል።


"ቢማላብ ኢትዮጵያ" የተሰኘው ይህ መርሃ ግብር "ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ " በተሰኘ ድርጅት የሚደገፍ እንደሆነ ሠምተናል።

በመርሃ ግብሩ የሚሳተፉ 15 መፍትሔ ፈጣሪዎች መመረጣቸው የተጠቀሰ ሲሆን የተለያዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ በመጨረሻም አሸናፊዎቹ የገንዘብ ተሸላሚ እንደሚሆኑ ተነግሯል።


ከተሳታፊዎቹ መካከል 11ዱ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች ናቸው የተባለ ሲሆን አራቱ ደግሞ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መሆናቸው ታውቋል።


"በኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ" የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አቤል ታደለ ቢማላብ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ መፍትሔዎችን ለማምጣት ያለን ቁርጠኝት ማሳያ ነው ብለዋል።



ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz



bottom of page