top of page

ህዳር 16፣2017 - ተቆፍረው የተተውና ጉድጓዶች ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆነው መቀጠላቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Nov 25, 2024
  • 1 min read

ከመርካቶ የጀመረውን የደረሰኝ ግብይት ላይ የሚያደርገውን ቁጥጥር 250 ባለሞያዎችን በማሰማራት በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች እየሰራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ፡፡


በከተማዋ ባሉ ሁሉም ስፍራዎች ግብይቶች ያለ ደረሰኝ እንዳይፈፀሙ ለማድረግ የቁጥጥር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የሚናገረው ቢሮው ከዚህ ጋር በተያያዘ በመርካቶ አካባቢ ከተፈጠረው ውዥምብር ወዲህ በመርካቶ የንግድ እንቅስቃሴው ምን መልክ አለው?


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ፤ #መርካቶ አካባቢ ያለው የንግድ እንቅስቃሴ በአብዛኛው ጥሩ ነው ነገር ግን አልፎ አልፎ ሱቆችን መዝጋት፣የቁጥጥር ባለሙያዎች በማይኖሩባቸው ሰዓታት ማታ እና በጣም በጠዋት ግብይት የመፈፀም ዝንባሌ እንዳለ ነግረውናል፡፡

ree

ከዚህ በኋላ በከተማዋ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ በመስተዳድሩ የተቋቋመው የኑሮ ውድነትና የህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ግብረሃይል ባሰማራቸው በእነዚህ ባለሙያዎቹ የቁጥጥር ስራ ይሰራል፤ ያለ #ደረሰኝ ሲሸጥ ተገኘ 100 ሺህ ብር ይቀጣል፤ ይህንን ተግባር ከቀጠለበት ቅጣቱም እየጨመረ ይሄዳል፡፡


ከተደጋገመ ነጋዴው ሌላ ማጣራት ይደረግበታልም ብለውናል የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ሰውነት ፡፡


የአቶ ሰውነት ገለፃ ነጋዴዎች ከዚህ ቀደም ያለደረሰኝ ገዝተውት #በመጋዘን ያስቀመጡት ንብረት ካለ ዓይነቱን፣ መጠኑን፣ የተገዛበትን ዋጋ ግብር ለሚከፍልበት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በማሳወቅ እቃውን ሲሸጡ ግን በደረሰኝ እንዲሸጡ ከዚያም ግብር በሚከፍሉበት ወቅት ያለደረሰኝ የገዙት እቃ በሚከፍሉት ግብር ላይ ታሳቢ እንዲደረግላቸው የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ የአሰራር ሥርዓት ዘርግቷል፡፡


ነጋዴዎችም ቢሆኑ ያለ ደረሰኝ ለመሸጥ የሚሞክሩ አምራች፣ አስመጪና አከፋፋዮች ካሉ ይጠቁሙኝ፤ ማህበረሰቡም የትኛውንም እቃ ሲገዛ ደረሰኝን በመቀበል የከተማዋን ገቢ ለመጨመርና ንግዱን ሥርዓት ለማስያዝ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ቢሮው ጠይቋል፡፡


Recent Posts

See All
ታህሳስ 3/2018 የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል ፍጆታ ካለፈው ሃምሌ ወር ወዲህ እያደገ መጥቷል ተባለ።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ምንጮች ከምታመርተው የኤሌክትሪክ ሃይል 90 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል እንደሆነ ተጠቅሷል። በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት ኢትዮጵያ ከውሃ እና ከነፋስ ከ15,300 ጊጋዋት ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨቷ ተነግሯል። በየወሩ በአማካይ 3,800 ጊጋዋት ሰአት የኤ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page