top of page

ህዳር 10፣2017 - ‘’በመርካቶ ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ተገንዝበናል’’ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

  • Nov 19, 2024
  • 1 min read

‘’በመርካቶ ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ተገንዝበናል’’ ከንቲባ አዳነች አቤቤ


‘’በመርካቶ ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል’’ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡


‘’ #በመርካቶ ህጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው #ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡


እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በጥናት ላይ የተደገፈ ክትትል ሲደረግ እንደነበረ አንስተው፤ በርካታ ህገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንደተገኙም አስረድተዋል፡፡

‘’ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን’’ ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ከ #ትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


በከተማዋ የታሪፍ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ፤ ከታሪፍ በላይ ባሰከፈሉ 1,066 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋልም ብለዋል፡፡


በተጨማሪም በተሸከርካሪዎች ውስጥ ታሪፍ መጠን ሳይለጥፉ የቀሩ 4,020 ተሸከርካሪዎችም ተቀጥተዋል ተብሏል፡፡


ከንቲባ አዳነች ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው እያደረገ ባለበት መድረክ ነው፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Recent Posts

See All
አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ።

ሐምሌ 22 2018 አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ማጠናከርና የፀረ-ተሕዋስያን መድኃኒቶችን አጠቃቀም ቁጥጥር ማጠናከር እንዲሁም የፋርማሲ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ማሳደግ ያስፈልጋል ተባለ። አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ኢትዮጵያ በመድኃኒት ምርት ራሷን መቻል እንዳለባት፣ በተ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page