top of page

ጥቅምት 7 2018  - ኢትዮጵያ በተለያዩ ተቋማት ለሚዘረጉ መሠረተ ልማቶች እስከ አሁን ማስተር ፕላን እንደሌላት ተነግሯል

  • Oct 17, 2025
  • 1 min read

አሁን ማስተር ፕላኑን የማዘጋጀቱ ስራ እንደተጀመረም ሠምተናል።

 

ከመሰረተ ልማት ዘርጋታ ጋር በተገናኘ እያጋጣሙ ያሉ ችግሮች አንዱ መነሻ ዘርፉን የተመለከተ ማስተር ፕላን አለመኖር እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተናግሯል።

 

የትኛው መሰረተ ልማት በየት በኩል ይለፍ፣ የትኛውስ ምን ቦታ አገልግሎት ይስጥ? የሚለው በዚህ ፕላን የተደገፈ አይደለም ሲሉ፤   የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያ በዴቻ ተናግረዋል።

 

አሁን ይህን ማስተር ፕላን ለማዘጋጀት ስራዎች ተጀምረዋል ያሉን አቶ ኢትዮጵያ መሰረተ ልማቶቹን የሚዘረጉ ተቋማት በስራው መሳተፋቸውንም ነግረውናል።

 

ተቋማቱ ማስተር ፕላኑን በማዘጋጀቱ ሂደት ከመሳተፍ ባሻገር ሃብት እና ባለሞያ ማዋጣታቸውንም ጠቅሰዋል።

 

በስራው እየተሳተፉ ያሉ ሞያተኞች ማስተር ፕላኑን የማዘጋጀቱን ተግባር ከግማሽ በላይ ከውነዋል ያሉን ስራ አስፈጻሚው ፣ ቢበዛ እስከ ሁለት ዓመት ባለ ጊዜ ይጠናቀቃል ሲሉ አክለዋል።

 

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ተቋማት መሰረተ ልማት ሲዘረጉ የተናበበ አካሄድ እንዲከተሉ የማስተባበሩን ስራ እንደሚሰራም ነግሮናል።

 

ንጋቱ ረጋሣ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

Recent Posts

See All
የነሐሴ 4 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሳውዲ_አረቢያ በሳውዲ አረቢያ ጂዛን በሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከባድ ቃጠሎ ተቅስቅሶ ነበር ተባለ፡፡ በጂዛኑ ማጣሪያ ላይ ቃጠሎ ተቅስቅሶ የነበረው ከባድ ፍንዳታ ከተሰማ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በጁቢየል የተፈጥሮ ጋዝ ማሰናጃ ከተማም ቃጠሎ ተቀስቅሶ ነበር ተብሏል፡፡ የሳውዲ ምንጮች ቃጠሎዎቹ ተቀስቅሰው እ

 
 
 
በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡

ነሐሴ 4 2018 በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት በበኩሉ ሳያጠፋ የምንቀጣው አሽከርካሪ የለም እንዲያውም ሁሉንም ህጎች እናስከብር ብንል የማይቀጣ አሽከርካሪ አይኖርም ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ምህረት ስዩም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page