top of page

ጥቅምት 14፣2017 - በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ60,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Oct 24, 2024
  • 1 min read

በአማራ ክልል የወባ ወረርሽኝ ሥርጭት ሰፍቶ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ60,000 በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተነገረ፡፡


ይህንን የተናገረው የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው፡፡

ከሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ600,000 በላይ ሰዎች በወባ የተያዙ መሆናቸውን ሪፖርት ያሳያል ብሏል ኢንስቲትዩቱ፡፡


የአዊ ዞን፣ የደቡብ ጎንደር ዞን፣ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ የምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በቅደም ተከተላቸው ወረርሽኙ ከፍተኛ ስርጭት የሚታዩባቸው አካባቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡


የኢንስቲትዩቱ የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንክር አሁን በክልሉ ያለው የወባ ወረርሽኝ ካለፉት 5 ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ማሳየቱን ይናገራሉ፡፡


በዚህም በአጠቃላይ በክልሉ 612,000 በወባ የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን የተነገረ ሲሆን ወረርሽኙ እንደ ክልል ብቻ ሳይሆን እንደሀገር እየጨመረ መምጣቱን አቶ ዳምጤ አስረድተዋል፡፡


ወረርሽኙ ካለፉት ዓመታት የተለየ ጭማሪ የማሳየቱ ምክንያት፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ከግንዛቤ መፍጠር ጋር በተገናኘ ጠንካራ ስራ አለመሰራቱ፣ የማህበረሰቡ የአጎበር አጠቃቀም ዝቅተኛ መሆን እና ሌሎችም ይነሳሉ ብለዋል፡፡


ክልሉ አሁን የገጠመውን #የወባ_ወረርሽኝ ለመቆጣጠር የሚያስችለው በቂ የመድሀኒት አቅርቦት አለ የሚሉት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ነገ እና ከነገ በስቲያ ወረርሽኙ በዚሁ መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ግን አቅማችን ይዳከማል ይላሉ፡፡


ካሳለፍነው ሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሶስት ወራት ውስጥ በወባ በሽታ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 37 ደርሷል ተብሏል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Σχόλια


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page