top of page

ግንቦት 30፣2016 - የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ

የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ፡፡


የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016 - 2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ ተነግሯል፡፡


የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም፣ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎች፣ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም በጀቱ እንዲዘጋጅ ተደርጓል ተብሏል፡፡


በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡


በጀቱ ለአንድ ትሪሊዮን ብር የተጠጋ ተብሎ ቢጠቀስም ስንት እንደሆነ ግን በዝርዝር አልተገለፀም።


ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላ ሚንትርጽ /ቤት ተናግሯል፡፡


ሰኔ 30 የሚጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት በጀት 801.6 ቢሊዮን ብር አንደነበር ይታወሳል፡፡

Comentarios


bottom of page