top of page

የካቲት 5 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም አለ

ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ የበጀት ዓመት ስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት አልደረሰብኝም አለ።

 

በዚሁ የስራ አፈፃፀም የግዜ ማዕቀፍ 6 ሚሊዮን ገደማ ደንበኞች አፍርቻለሁ ብሏል። በአጠቃላይ የደንበኞቼ ቁጥርም 80.5 ሚሊየን ደርሰዋል ብሏል።

 

ኩባንያው በስድስት ወር የስራ አፈፃፀሙ  61.9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የተናገረ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ 43.3 በመቶ ወይም 18.9 ቢሊዮን ብር እድገት አሳይቷል ተብሏል።

 

ገቢውም የእቅዱን 90.7 መሆኑን ተናግሯል።

 

ይህ የተሰማው ኩባንያው  የስድስት ወር የስራ አፈፃፀሙን በተናገረበት ግዜ ነው።

 

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዘንድሮ ግማሽ በጀት ዓመት አዳዲስ ምርትና አገልግሎት ከማምጣት ባለፈ ከከተማ አልፎ በገጠር አካባቢ የኔትዎርክ ሽፋን ማድረሱን ተናግረዋል።


44 አዲስ ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች ቀርቧል ተብሏል።

 

ከማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ ጋር በተገናኘ 354 አገልግሎቶች ምንም አይነት የዋጋ ማሻሻያ እንዳልተደረገባቸው ተሰምቷል።

 

አፈፃፀሙ ከቴሌኮም መሰረተ ልማት  ባለፈ የዲጅታል መሰረተ ልማቱንም የተመለከተ ነው ተብሏል።

 

በዲጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ መዓዘንም 4.2 ሜጋ ዋት ያለው የሞጁላር ዳታ ሴንተር ና ክላውድ መገንባቱ ተሰምቷል።

 

በዚህም አገልግሎትም 18 ባንኮችና የ መንግስት ተቋማት እንደሚጠቀሙበት ታውቋል።

 

በስድሰት ወሩ 18ሺ ደንበኞች ምንም ወጭ ሳይጠየቁ  በፊክስድ ኔትዎርክ የኢንተርኔት አገልግሎት መአዘን ከኮፐር ወደ ፋይበር ተገናኝቶላቸዋል ተብሏል።

 

ይህ በመሆኑ ለደንበኞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት እንዲያገኙ አግዟቸዋል ተብሏል።

 

ከኔትዎርክ መሰረተልማት በኩል 119 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሆን ተጨማሪ የፋይበር ግንባታ ተደርጓል።

 

የኩባንያው የሞባይል ኔትዎርክ ጣቢያ 8 ሺህ 529 መድረሱ ተሰምቷል።

 

ኩባንያው የቢዝነስ ተቋም ቢሆንም በራሱ ወጪ በገጠር አካባቢ ያለውን ደንበኛ ለመድረስም 81 የሞባይል ጣቢያ ማስፋፊያዎችን ማድረጉን ተናግሯል።

 

ኢትዮዽያን ከሌላ ሀገር የሚያገናኝበት ጌት ወይ መሰረተ ልማትም ፈጣንና የተሻለ እንዲሆን ማስፋፍያ ተደርጎለታል ተብሏል።

 

በአሁኑ ሰዓት ኢንተርኔት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው  በ5 መስመር  መሆኑን ያስረዱት ስራ አስፈፃሚዋ እነሱም ሱዳን፣ ጂቡቲ በሁለት በኩል፣ በሶማሌላንድ እና ኬኒያ ናቸው ብለዋል።

 

በስድስት ወሩ 67 ከተሞች ተጨማሪ የ 4ጂ አገልግሎት አግኝተዋል  እስካሁንም 491 ከተሞች የ 4ጂ ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል።

 

በስድስት ወር ስራ አፈፃፀም 8 ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት አግኝተዋል ተብሏል።

 

ከማስፋፍያ ጎን ለጎን በግጭት ምክንያት  ጉዳት የደረሰባቸው 231 የሞባይል ጣቢያዎች ዳግም ጥገና ተደርጎላቸዋል ተብሏል።

 

በስድስት ወር ውስጥ ምንም አይነት ትርፍ ያልተጨመረበት 50ሺ የሞባይል ቀፎዎች ለደንበኞች መቅረቡን ኩባንያው አስረድቷል።

 

የደንበኞቼ ብዛት 80.5 ሚሊዮን ደርሰዋል ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ከሀገሪቱ ህዝብ 99.1 በመቶ እንዲሁም ከሀገሪቱ አካባቢዎች ደግሞ 85.4 በመቶውን አዳርሻለሁ ብሏል።

 

ተህቦ ንጉሴ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page