ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን በመከላከል በሐምሌ ወር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሥነ ሕዝብ ድርጅት እውቅና ማግኘቷ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ያገኘችው ይሄው እውቅናም ከአፍሪካ ሀገሮች የመጀመሪያ እና ብቸኛ ያደርጋታል ተብሏል፡፡
ትናንት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በሴቶች ላይ የሚደርሱ #ጎጂ_ልማዳዊ_ድርጊቶች እንዲቀንስ የበኩላቸውን ከውነዋል የተባሉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅውና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ለመሆኑ ኢትዮጵያ በሴት ልጅ #ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻ ላይ ምን ስለሰራች ነው ይህንን እውቅና ያገኘችው?
ለኢትዮጵያ የተሰጣት እውቅና በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን ጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ቀንሳለች በሚል ሳይሆን ያለ እድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን የማስቀረት ባደረገቸው ጠናካራ ስራ ነው ሲሉ የብሔራዊ ጥምረት የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አበባው ቦጋለ ነግረውናል፡፡
በ2025 ዓ.ም ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛትን እና #ያለ_እድሜ_ጋብቻን ላመስቆም እሰራለሁ ብላ ቃል የጋባችው እንደ እ.ኤ.አ በ2015 ነበር፡፡
ነገር ግን ያንን ማድረግ ስላልቻለች ለቀጣዮቹ ስድስት አመታት ለማራዘም ውጥን መያዟን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡
መንግስት፣ የሀይማኖት ተቋማት እና ሌሎች የሚመለከታቸው በሀላፊነት ስራዎችን የሚከውኑ ከሆነ የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን ይጠፋል ብለን እናምናለን የሚሉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ከዚህ ቀደም ስራዎችን ስንሰራ በነበሩበት አመታት እንደ ኮቪድ ያሉ ችግሮች እንቅፋት ሆነውብናል ብለዋል፡፡
የሴት ልጅ ግርዛትን እና ያለ እድሜ ጋብቻ በገጠሪቱ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስፋት የሚታይ ቢሆንም በከተሞች ላይም ችግሩ እንደሚስተዋል የሚነገር ነው፡፡
ድርጊቱን ፈፃሚዎች ላይ የሚጣለው የህግ ቅጣት ደግሞ ሌላኛው ችግሩ በሚፈለገው መጠን እንዲቀንስ ከማያደርጉት ነገሮች አንዱ ነው የሚሉት አቶ አበባው በተለይ ያለውን ህግ በትክክል ተፈፃሚ እንዳይሆን ማድረግ ላይ ደግሞ ሰፊ ክፍተት አለ ይላሉ፡፡
ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ 40 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ያለ እድሜአቸው እንደሚያገቡ ጥናት ያሳየ ሲሆን የሴት ልጅ ግርዛት ደግሞ 65 በመቶ እንደነበር ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያ ይህንኑ ችግር ለመቀነስ እሰራለሁ ብላ ከገባቸው ቃልኪዳን በኋላስ እነዚህ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ምን ደረጃ ላይ ደርሰዋል የሚለውን ለማወቅ ሀገራዊ ጥናት እየተጠና መሆኑን ሸገር ሰምቷል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments