top of page

ታህሳስ 5፣2017 - በጥር ወር 1,000 ጥንዶች ሊሞሸሩ ነው

በ2017 ዓ.ም በጥር ወር 1,000 ጥንዶች ሊሞሸሩ ነው።


በአንድ ቀን 1000 ጥንዶችን የሚሞሽረው ያሜንት ኃ/የተ/የግ/ማ ሲሆን ከቀደሙት ኩነቶች በተሻለ መልኩ 1000 ኢትዮጵያን ጥንዶች እንዲሁም 250 ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ጥንዶች የሰርግ ስነ ስርዓቶቻቸውን ባህላዊ ይዘታቸው ተጠብቆ እንደሚካሄድ ተነግሯል።


‘’የሺህ ጋብቻ’’ ላይ የአለም አቀፋዊ #ቱሪስቶችን ትኩረት ለመሳብ የሚችሉ ማህበራዊና ባህላዊ ትዕይንቶች ይቀርቡበታል ተብሏል።

ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ ይሞሸራሉ፣ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት የሺህ ጋብቻ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላታል መባሉን ሰምተናል።


#የሺ_ጋብቻ ፕረግራሙን ሲያሰናዳ የዘንድሮው ለ3ተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል ድርጅቱ ስለ የሺ ጋብቻ አላማ እና አጠቃላይ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ያደርሱልኛል ያላቸውንም ሁለት ጥንዶች አምባሳደር አድርጎ የሾመ ሲሆን አርቲስቶቹ ጥነዶች ይገረም ደጀኔ እና ጽዮን ዮሴፍ አንደኞቹ ናቸው።


በተጨማሪም አርቲስቶቹ ተስፋለም ታምራት እና ቃልኪዳን አበራም የየሺ ጋብቻን አላማ እና ተያያዥ ሀሳቦችን ለማህበረሰቡ ያደርሳሉ ብዬ ስላሰብኩ መርጫቸዋለሁ ብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page