top of page

ታህሳስ 24፣2017 - የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አዲሱን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አዲሱን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑ ተነገረ፡፡


በከተማዋ የሚከሰቱ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 በስራ ላይ ሊውል ነው ተብሏል፡፡


በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአውቶማቲክ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ሥርዓት እና ዘመናዊ የፓርኪንግ ሲስተም እንዲሁም የተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡


ዛሬ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የትራፊክ ደንብ ጥሰት ቁጥጥርና የፓርኪንግ አስተዳደር ሥረዓት ሥራ ማስጀመሪያ መረሃ-ግብር በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ነው፡፡


በአዲሱ የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016ን ተግባራዊ ለማድረግ ባለስልጣኑ ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ስልጠና ሰጥቶ ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡


በተጨማሪም በቅርቡ የበለጸገውን አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት እና ትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተም መተግበሪያ የትራፊክ ግጭት ሲደርስ ወዲያውኑ በሲስተሙ አማካኝነት አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል እና አሽከርካሪዎቾ በቀላሉ የፓርኪንግ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ የሚጠቁም መሆኑን ተነግሮለታል፡፡


የተለያዩ ማሻሻዎች የተደረጉለትና የሚፈጸሙ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል የተባለው ደንብ የትራፊክ ቅጣት የገንዘብ መጠኑ ከፍ የተደረገበት እና ለመጀመሪያ ደረጃ እርከን ጥፋቶች ከ500 ብር ጀምሮ ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ እርከኖች ከ1,500 እስከ 3,000 ብር ድረስ ቅጣት የሚጥል ነው ተብሏል፡፡


ምህረት ስዩም

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page