በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ።
- Mar 11
- 1 min read
መጋቢት 1/2018
በጋሞ ዞን የጎርፍ ናዳ 30 ሰዎችን ገደለ።
በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ስዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ተናግሯል።
የዞኑ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረኩ ነው ብሏል።

የ30 ህይወት የቀጠፈው የጎርፍ አደጋ መቼ እንዳጋጠመ ዞኑ ያለው ነገር የለም።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ "በጋሞ ዞን በደጋማ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት ናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በራሴና በክልሉ መንግስት ስም እገልጻለሁ"ብለዋል።
እንደ አርባ ምንጭ እና ገረሴ ከተሞች ባለፋት ሁለት ቀናት በአካባቢዎቹ እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛልና ተጠንቀቁ የሚል መልዕክት ሲያወጡ ነበር።
መንገዶች ላይ በናዳ መዘጋትና መሻገሪያ ድልድዮች ላይ ጎርፍ የመሸፈን ችግር እያጋጠመ በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ይጠንቀቅ የሚል ማስታወቂያ አውጥተዋል።





Comments