top of page

ሰኔ 18፣ 2016 - የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን የተዘጋጀው አዋጅ ከዚህ በፊት ካሳ ያልተከፈላቸውን አያካትትም ተባለ

የመሬት የዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን የተዘጋጀው አዋጅ ከዚህ በፊት ካሳ ያልተከፈላቸውን ሰዎች አያካትትም ተባለ።

 

ይህ የተባለው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረገው 34ተኛ መደበኛ በስብሰባ ላይ ነው።

 

አዲሱ አዋጅ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺዎችን አያካትትም፡፡

 

የምክር ቤት አባላት ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

 

ከዚህ ባለፈም ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል የሚል ጥያቄ ሌላ የምክር ቤት አባል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ከዚህ በፊትም ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋታቸውም የምክር ቤት አባሉ አንስተዋል፡፡

 

አንዳንድ የፍርዴቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍርድቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ሲሉ አንድ የምክር ቤት አባል ጠይቀዋል፡፡

 

ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ያሉት የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዋ አዲሲ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ ነው ብለዋል፡፡

 

ክልሎች አካባቢ ያለው የበጀት ጉድለት እንዳለ ሆኑ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ ነው፡፡

 

ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል እንዳሉት ይህ ውሳኔ ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው ይላሉ፡፡

 

የመሬት የዞታ የሚለቀቅበት ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን የተዘጋጀው አዋጅ  ምክር ቤቱ አፅድቆታል፡፡

 

በረከት አካሉ

 

 

 

Comments


bottom of page