በመዲናና ዘለሰኛ ስልት ስመ ገናናውና ታዋቂው ሙዚቀኛ አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ከ6 ወራት በፊት በድንገት ወድቀው እግራቸው በመሰበሩ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በትናንትናው እለት መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ከሙዚቀኛው የቅርብ ወዳጅ ሆኑት መጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ሰምተናል፡፡

በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋጭነታቸው የሚታወቁት ሙዚቀኛው አለማየሁ ፋንታ ስራቸውን የጀመሩት ሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት በመቀጠር ነው፤ እዚያም ለ10 ዓመታት ሰርተዋል፡፡
ባህላዊዎቹን የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያዎች በገናን በመደርደር፣ ክራርና መሰንቆን አሳምረው በመጫወት ይታወቁ እንደነበር መጋቢ ብሉይ አለሙ አጋ ነግረውናል፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ የቀለም ትምህርትን የተማሩ እንዲሁም የ #ድቁና ትምህርትም የነበራቸው ነበሩ፡፡
ስርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ፒያሳ በሚገኘው በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈፀምም ሰምተናል፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ አለማየሁ ፋንታ ባለ ትዳርና 6 ልጆች አባት ነበሩ፡፡
ምንታምር ፀጋው
Комментарии