መስከረም 6 2018 - በኢትዮጵያ በአዲሱ ዓመት ስለ ሠላም ከመመኘት ያለፈ ቁርጠኛ ስራ ይጠይቃል ተባለ።
- sheger1021fm
- Sep 16
- 1 min read
ኢትዮጵያ የጠንካራ ሀገረ መንግስት ታሪክ ያላት ሀገር እንደ መሆኗ ሁሉ ጠንካራ የተቃዋሚ ኃይሎች ታሪክ ያላት ሀገር በመሆኗ ሠላምና መረጋጋትን ለማምጣት በአዲሱ ዓመት ስለ ሠላም ከመመኘት ያለፈ ቁርጠኛ ስራ ይጠይቃል ተባለ።
የሀገርን ሠላምና መረጋጋት በማምጣት ሂደት ውስጥ ሰፊ ድርሻ ያላቸው የሲቪክ ማህበራት፤ ሠላምን በማስፈን በኩል የሚሰሩት ስራ በተበታተነ አደረጃጀትና በተናጠል ነው የተባለ ሲሆን ከዚህ በኋላ በተጠናከረ ህብረት ለሰላም መቆም አለባቸው ሲባልም ሰምተናል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ነው።
ኮንፈረሱ "በአዲሱ ዓመት ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣የሲቪክ ማህበራት፣የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና ሌሎች ተሳትፈውበታል።
መድረኩ ሁሉንም የሚመለከታቸውን በማሰባሰብ ለሰላም መደፍረስ ዋና ዋና ምክንያቶች ላይ ለመወያየት፣ በሰላም ግንባታ ጥረቶች የተገኙ ውጤቶችን ለመዳሰስ፣ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ የወደፊት ጉዞን በትብብር ለማቀድ የተዘጋጀ መድረክ ነው ተብሏል።
ንጋት መኮንን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments