መስከረም 23፣2017 - ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የኑሮ ጫናውን መቋቋም እንዲችሉ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በካቢኔ ፀደቋል ተባለ
- sheger1021fm
- Oct 3, 2024
- 1 min read
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የኑሮ ጫናውን መቋቋም እንዲችሉ የተደረገው የደመወዝ ጭማሪ በካቢኔ ፀደቋል ተባለ፡፡
የደመወዝ ማሻሻያው ከያዝነው መስከረም ወር ጀምሮ ይተገበራልም ተብሏል፡፡
ይህን ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ናቸው፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ትግበራ አስመልክተው በሰጡት ማብራርያ ነው፡፡
ለደመወዝ ጭማሪው ከ91 አስከ 92 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ነው ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፡፡
ይህም በተጨማሪ በጀትነት የሚታወጅ ይሆናል ተብሏል፡፡
የደሞዝ ጭማሪው የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት ሰራተኞችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለመንግስት ሰራተኛው የኑሮውን ጫናውን ለማቃለል ታስቦ መንግስት የተገበረው ነው ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
የደመወዝ ጭማሪው በቅርቡ በሲቪል ሰረቪስ ኮሚሽን በኩል ይፋ እንደሚደረግ የገንዘብ ሚኒሰቴር አስርድቷል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments