ሐምሌ 4፣ 2016 - የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ
- sheger1021fm
- Jul 11, 2024
- 1 min read
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ፡፡
ከዛሬ ሐምሌ 3፣ 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎል።

የአለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠነኛ የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈልጓል ሲል የነግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በዚህም መሰረት:-
ቤንዚን ከነበረበት 78.67 ብር በሊትር ወደ ብር 82.60 በሊትር ክፍ ብሏል፡፡
ነጭ ናፍጣ ከነበረበት 79.75 ብር በሊትር 83.74 ብር በሊትር ሆኗል፡፡
ኬሮሲን …. 83.74ብር በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ … 70.83 ብር በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…… 65.48 ብር በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ……… 64.22 ብር በሊትር ሆኗል።
ንጋቱ ሙሉ
Comments