top of page

ሐምሌ 25፣2016 - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስለ ሰሞኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ዛሬ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስለ ሰሞኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ዛሬ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


ስለ ጉዳዩ ፍንጭ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ትናንት ለፓርላማ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡


የገንዘብ ሚኒስትሩ የት እና እንዴት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማብራርያ እንደሚሰጡ ግን አላብራሩም፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማሻሽያው ላይ ቁጥጥር ስለሚስፈልጋው ጉዳዮች ስለ ፖሊሲው ዓላማ እና ለህዝብ ይደረጋል ስለተባለው ድጎማእንዲሁም ድጋፍ ዝርዝር ጉዳይ ማብራርያ እንደሚሰጡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ትናንት ለፓርላማ አባላት አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page