top of page

ሐምሌ 25፣2016 - ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ‘’ሽልማት ጣመኝ ፔፕሲ ድገመኝ’’ ሲል በጠራው የሽለማት መርሃ ግብር 9 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ሊሸልም ነው

በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ከሚተዳደሩ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ‘’ሽልማት ጣመኝ ፔፕሲ ድገመኝ’’ ሲል በጠራው የሽለማት መርሃ ግብር 9 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ሊሸልም ነው፡፡

 

ኩባንያው በምርት ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች ፈትቶ ወደ ገበያው ከተመለሰ በኋላ የምርቶቼ ደንበኞች በደስታ ተቀብለውኛል ለዚህም ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኙ እድሎችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል አስረድቷል፡፡

ሞሃ የሚያመርታቸውን ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና 7 አፕ የጠርሙስ ለስላሳ መጠጦችን የሚጠጡ እና እድለኛ የሆኑ ሰዎች 9 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ይሸለማሉ ሲሉ የኩባንያው የማርኬቲንግ ሀላፊ አቶ ንጉሱ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡

 

6 BYD seagull መኪናዎች፣ 3 id 4 Volkswagen መኪናዎች፣ 12 የኤልክትሪከ ሞተር ብስክሌቶች፣ 100 ስማርት ስልኮች እና 1 ሚሊዮን ነጻ መጠጦች ለሽልማት ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡

ሽልማቱም ለመጪዎቹ 3 ወራት ይቆያል ተብሏል፡፡

የሽልማቱ አሸናፊዎች ቆርኪው በመላጥ ማወቅ ይችላሉ ያሉት አቶ ንጉሱ፤ ሽልማቱ የተዘጋጀው በፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና 7 አፕ የጠርሙስ ምርቶች ላይ መሆኑንን ጠቅሰዋል፡፡

 

ሞላ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ 3፣ በሀዋሳ፣ በመቀሌ፣ በበደሌ፣ በቡሬ እና ጎንደር ደግሞ አንድ አንድ በአጠቃላይ 8 ፋብሪካዎች እንዳሉት ተናግሯል፡፡

 

በፀጥታ ችግር ምክንያት ምርት ካቆመው የቡሬው ፋብሪካ ውጭ ሁሉም እያመረቱ ነው ተብሏል፡፡

 

ወርሃዊ የምርት መጠኑም 4 ሚሊዮን ሳጥን(ካሣ) መሆኑን መሆኑን ሰምተናል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

 

Comments


bottom of page