top of page

ሰኔ 20፣ 2016 - ለምን ይሆን የኢንሹራንስ ተቋማት ለግብርናው ዘርፍ የመድህን ሽፋን ለመስጠት የማይደፍሩት?

ገበሬው አንዴ በግሪሳ ወፍ፣ ሌላ ጊዜ በበረሃ አንበጣ እና በመሳሰሉት የሰብል ተባዮች ምክንያት የዘራው ዘብል ገና አውድማው ላይ ይወድምበታል፡፡


ሰብሉ ደርሶ ለመሰብሰብ ሲደርስም ድንገተኛ ዝናብ፣ የእሳት አደጋ እና ሌሎች ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች የደረሰው ሰብል ሲያወድሙት ይታያል፡፡


የግብርና ሚንስቴር ባወጣው መረጃ መሰረት የሰብል ተባዮችን ለማጥፋት ባለፉት 3 ዓመታት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡


በትግራይ ክልል በበጋ መስኖ ለምቶ የነበረ 114 ሄክታር የስንዴ ምርት እና የማሽላ ምርት ሙሉ ለሙሉ በወፎች ወድሟል፡፡


ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ ለገበሬው ካሳ የሚከፍለው፣ ለጠፋው ንብረት ምትክ የሚሠጠው የኢንሹራንስ ኩባንያ የለም፡፡

በዚህም ምክንያት ገበሬው ለፍቶ መና ሲቀር በተደጋጋሚ ይስተዋላል፡፡


ታዲያ ለምን ይሆን የኢንሹራንስ ተቋማት ለግብርናው ዘርፍ የመድህን ሽፋን ለመስጠት የማይደፍሩት?



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page