‘’የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ፤ ህዝብ በመንግስት ተቋማት አመራሮች ምደባ ላይ ሊኖረው የሚገባውን ተሳትፎ የሚገደብ ነው’’ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተቸ፡፡
በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ላይ #የኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ተቋማት እና የመገናኛ ብዙሃን የስራ ሃላፊዎች የሰላ ትችት አቅርበውበታል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ትችቱ የቀረበው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጠራው ይፋዊ የህዝብ ውይይት ላይ ነው፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች አዋጁን በዚህ ፍጥነት ለማሻሻል ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ፍላጎቱ የመጣው ከመንግስት ብቻ ነው እንዲሻሻሉ የቀረቡ አንቀጾችም የህዝብን #የመናገር_ነጻነት የሚገድቡ ናቸው የሚል ቅሬታ በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል፡፡
ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት እንደመጡ የተናገሩ አቶ መሰረት አታላይ የተባሉ የውይይቱ ተሳታፊ ‘’አዲሱ ማሻሽያ ረቂቅ ከነፃነት ተመልሰን ወደ ሸምበቆ ውስጥ የምንገባበት እና እንደንፈናፍን ማሰሪያዎች ቀደመው የተዘጋጁበት እንቀጾች የተካተቱበት ነው’’ ሲሉ ተችተዋል፡፡

አቶ ቁምላቸው ዳኜ የተባሉ ከሴቶች መብት ተሟጋቾች ድርጅት እንደተወከሉ የተናገሩ #የህግ_ባለሞያ በበኩላቸው በስራ ላይ ያለው የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ሲወጣ በቂ ጥናት ተደርጎበት መውጣቱን አስረድተው በዚህ ፍጥነት እና በቂ ውይይት ሳይደረግበት አዋጁን ለማሻሻል ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ሌላው ከኢሳት ነፃ የህዝብ ሚዲያ እንደተወከሉ የተናገሩት አቶ አበበ በጎላ ተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡
እሳቸውም ‘’የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ ከ #ዴሞክራሲ_ተቋማት ውስጥ አንዱ ነው ብዬ አስባለው አሁን በተፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታ ዘለን ለዴሞክራሲ እድገት ጥሩ አጋጣሚ የሚሰጡ ህጎችን መገደብ የምንጀምር ከሆነ እዚህ ላይ ላይቆም ይችላል ወደ ሰብአዊ መብት ተቋማት እና ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምም እንዳይሄድ ስጋት አለኝ’’ ብለዋል፡፡
የኢሰመኮ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የቦርድ አባላት ስብጥር ላይ እንዲኖር የነበረው አንቀፅ መሻሻሉ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በበኩሉ በስራ ላይ ያለው አዋጅ ለባለስልጣኑ የመፈጸም ኃላፊነት የነፈገ ነው ብሏል፡፡
በስራ ላይ ያለው አዋጅ ከነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም መሆን ስላልቻለ ነው ያልተከበረው ሲል ባለስልጣኑ ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments