top of page
የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡
ግንቦት 26/2018 - ዓለም አቀፍ ወሬዎች #ኤልኒኖ የአለማችን የሙቀት መጠን በእጅጉ እየጨመረ እንደሚመጣ የሳይንስ ሊቃውንት አስጠነቀቁ፡፡ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በብዙ የአለማችን ክፍሎች እንደሚመዘገብ አለም አቀፉ የአየር ሁኔታ ተከታታይ መስሪያ ቤት ማስጠንቀቁን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ኤል ኒኖ የተሰኘው የአየር ለውጥ ክስተት የከፍተኛ ሙቀት ጭማሪው ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡ ከወዲሁም የሙቀት መጠን ጭማሪው መከሰቱን መረጃው አስታውሷል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ደግሞ የሙቀት መጠን ጭማሪው እየተጠናከረ ይመጣል ተብላል፡፡ የሙቀት መጠን ጭማሪው ደረጃ ሊቃውንቱን ከወዲሁ በእጅጉ እያሳሰበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የአየር ለውጡን ተፅዕኖ ለመገደብ ሲወተወት ቢቆይም ችግሩ ከእርምጃው እየገዘፈ መምጣቱ ይነገራል፡፡ #አሜሪካ የአሜሪካ ጦር በኢራን ኬሽም ደሴት ላይ ያነጣጠረ
8 hours ago


በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈው የትምህርት ዘመን ምን መፍትሔ ተበጅተውለት ይሆን?
ግንቦት 26/2018 የተጀመረው የትምህርት ዘመን ሊጠናቀቅ የ1 ወር እድሜ ቀርቶታል፡፡ በመፅሐፍ ህትመት ችግር ምክንያት፤ አንድ መፅሐፍ ለአራት ሲጠቀሙ የቆዩ ተማሪዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ የበጀት እጥረት እና የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልን ጨምሮ በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ያለፈው የትምህርት ዘመን ምን መፍትሔ ተበጅተውለት ይሆን? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. ፋሲካ ሙሉወርቅ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :- https://x.com/shegerfm?s
9 hours ago


በምርጫ ወቅት ከህግ ውጪ የሆነ ተግባር የፈፀሙ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ከስራ ማሰናበቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ።
ግንቦት 25/2018 በምርጫ ወቅት ከህግ ውጪ የሆነ ተግባር የፈፀሙ የምርጫ አስፈፃሚዎችን ከስራ ማሰናበቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የምርጫውን እለትና የድምፅ ቆጠራ እየተካሄደበት ነው ያሉትን የዛሬውን እለት ክንውን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው:። የተለያዩ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ የቦርዱ የክትትል ቡድን ባደረገው አሰሳ ከህግ ውጪ የሆነ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙ ምርጫ አስፈፃሚዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል። አድርገውታል የተባለው ህገ ወጥ ተግባር ባይፍታታም አዲስ አበባ ላይ ምርጫ ሲያስፈፅሙ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች ናቸው ከስራ ተባርረዋል የተባለው። በተያያዘም ቡርጂ በተባለ የምርጫ ጣቢያ ትናንት የምርጫ አስፈፃሚዎች የምርጫ ወረቀቱን ራሳቸው ሲሞሉ ተገኝተዋል በመባሉ ጣቢያው መዘጋ
11 hours ago


የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምሰጠው የአየር ትንበያ ትክክለኛነት እስከ 90 በመቶ እየደረሰ ነው አለ።
ግንቦት 21/2018 የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምሰጠው የአየር ትንበያ ትክክለኛነት እስከ 90 በመቶ እየደረሰ ነው አለ። እንደ ውሃና ኢነርጂ እንዲሁም ግብርና ሚኒስቴር ያሉ ተቋማትም ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ የትንበያ መረጃውን መሰረት አድርገው ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ነግረናል። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተለያዩ ወቅቶች የሚኖረውን የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተመለከተ ትንበያዎችን እና ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ይሰጣል። ኢንስቲትዩቱ እነዚህን ትንበያዎችን እና ማስጠንቀቂያዎች የሚሰጠው በተለያዩ አካባቢዎች ካሉት የአየር ሁኔታ መመዝገበያ ጣቢያዎች፤ከሚያሰባስበው መረጃ እንደሆነ የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል። መረጃዎቹን በመጠቀም የሚሰጠው ትንበያ ትክክለኛነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መ
5 days ago


የት/ት ጉዳይ ግድ ብሎናል ያሉ 4 ድርጅቶች ተናባቢ የዲጂታል የትምህርት ስነ ምህዳር ይዘው መምጣታቸውን ተናገሩ፡፡
ግንቦት 21/2018 የትምህርት ጉዳይ ግድ ብሎናል ያሉ 4 ድርጅቶች "አሪፍ ስኩል" ሲሉ የጠሩትን ተናባቢ የዲጂታል የትምህርት ስነ ምህዳር ይዘው መምጣታቸውን ተናገሩ፡፡ አሪፍ ስኩል ይዘው የመጡት አሪፍ ፔይ ፣ AIT ቴክሎሎጂ፣ ገበያ እና ኢዱኬሽን ማተርስ የተባሉ አራት ድርጅቶች ናቸው፡፡ አሪፍ ስኩል የተቀናጀ የትምህርት አስተዳደር ሥርዓትን ፣ የክፍያ መንገድን ፣ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የታገዘ የትምህርት መሳሪያዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ስርዓቱ ለትምህርት ቤቶች አስተዳደር ፣ ለመምህራን፣ ለተማሪዎች እንዲሁም ለወላጆች እንደሚጠቅም ሲነገር ሰምተናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ....... ንጋቱ ሙሉ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shortur
5 days ago


የእዳ ሽግሽግ ድርድሩ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ አለመጠናቀቁ ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ምን መሳይ ነው?
ግንቦት 21/2018 ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የተወሰደው የአንድ ቢሊዮን ዶላር እዳ አከፋፈል በተመለከተ ኢትዮጵያ ከአበዳሪዎቿ ጋር አልተስማማችም፡፡ ከሰሞኑም ለቀናት የተደረገው ንግግር ውጤት እንዳላመጣ የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ የእዳ ሽግሽግ ድርድሩ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ አለመጠናቀቁ ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ምን መሳይ ነው? የዘርፉን ባለሙያ አነጋግረናል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ....... ትዕግስት ዘሪሁን የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at
5 days ago


ተቋማት በየዓመቱ ከሚያገኙት ትርፍ፤ ምን ያህሉን ለሰራተኞቻቸው ያከፋፍላሉ?
ግንቦት 20/2018 አንዳንድ ተቋማት ከሚያገኙት ዓመታዊ ትርፍ ከፊሉን ለሰራተኞቻቸው በጉርሻ ወይም በደመወዝ ጭማሪ መልክ ያከፋፍላሉ፡፡ ሌሎች ተቋሞች ደግሞ የተለየ መንገድን ይከተላሉ፡፡ ስራ እንዳይበደል በአሰሪና ሰራተኛ መሀከል ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ተቋማት ምን ዓይነት መንገድን ቢከተሉ ይበጃል? የሌሎች ሀገሮች ልምድ እንዴት ያለ ነው? ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ....... ማርታ በቀለ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Website፡ https://www.shegerfm.com/ YouTube : https://shorturl.at/18TS1 Telegram : https://shorturl.at/68aeK Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4 WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx X :-...
5 days ago


የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ሙሉ ለሙሉ ለመስጠት የግብዓት እጥረት እንደገጠማቸው ያነጋገርናቸው ክልሎች ተናገሩ፡፡
ግንቦት 20/2018 የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይን ሙሉ ለሙሉ ለመስጠት የግብዓት እጥረት እንደገጠማቸው ያነጋገርናቸው ክልሎች ተናገሩ፡፡ ከሰኔ 24 ጀምሮ የሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ፈተና ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ማጠናቀቁን በተለያዩ ጊዜያት መነገሩ ይታወሳል፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ፤ በክልሉ ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል በኦንላይን መፈተን የሚችለው 76 በመቶ ብቻ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በቀሪ ጊዜ ይህንን ቁጥር ወደ 80 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ቢሮው የጠቀሰ ሲሆን ዘንድሮ 24 በመቶ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በወረቀት ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑን ነግሮናል፡፡ ለፈተናው የሚያስፈልጉ የኮምፒዩተር እጥረት፣ የኢንተርኔት አለመሟላት እና ሌሎች ግብአቶች እጥረት ማጋጠሙ ተሰምቷል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክል
6 days ago


የምግብ ችግር እያለባትም፤ ካመረተችው ግማሽ የሚጠጋውን የምትደፋዋ ኢትዮጵያ!
ግንቦት 20/2018 በኢትዮጵያ በየዓመቱ ገበሬው ከሚያመርተው ምርት ከ40 በመቶ በላዩ ከገበታ ሳይደርስ ባክኖ ይቀራል። በየዓመቱ ከሚመረት እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም ያለው ቶሎ የሚበላሽ የግብርና ምርት ግማሽ ያክሉ ተበላሽቶ የሚደፋ እንደሆነ ይነገራል። አፍሪካ በዚህ መንገድ ገበሬዎቿ ቢያመርቱም 4 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ምርት ተበላሽቶ መልሳ ትደፋለች። ከዚህ ጀርባ ያለው ትልቁ ችግር የቀዝቃዛ ምርት ማጓጓዣና መስቀመጫ ሰንሰለት አለመኖር ነው ይባላል። ያደጉት ሀገሮች ከአጠቃላይ ምርታቸው የምርት ብክነትን ከ1 በመቶ በታች ማውረድ ችለዋል። ኢትዮጵያ ግን የምግብ ችግር ቢኖርባትም፤ ዛሬም ብዙ ስለማምረት ብትደክምም ካመረተችው ግማሽ ያክሉን እየደፋች ቀጥላለች። ታዲያ ምን ይበጃል? የቀዝቃዛ ምርት ሰንሰለትን ማስፋፋትስ ለምን ከባድ ሆነ? የዘርፉ ባለሙያዎች
6 days ago



Facebook
Twitter
Pinterest
Tumblr
Copy Link
Link Copied
Search video...

Now Playing
እንደ ቤተሰብ - ዛሬም በኢትዮጵያ 40 ሺህ ህፃናት ከዚህ ችግር ጋር ይወለዳሉ'
57:31

Now Playing
በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
04:54

Now Playing
አልሰማንም እንዳትሉ - የፖለቲካ ሹም ሽር በፍርድ ቤት ይዳኛልን?
04:21

Now Playing
አሜሪካ ጫፌን የምትነካ ከሆነ ኬብሎቹን ቆርጬ የኢንተርኔት ስርዓቱን አስተጓጉላለው #shegerfm #iranisraelwar
07:32

Now Playing
ማሟሻ - የኔን መንግስት በመልካም ስላገለገለ ወዳጃችንን በኒሻናችን አክብረን ሾመን ሸልመነዋል #shegerfm #muamuasha
09:31

Now Playing
ስም አይቀበርም - ሠዓሊ ለማ ጉያ #Lemma_Guya
01:10:56

Now Playing
የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ከአንድ እቃ ላይ የሚያተርፉት ምን ያክል ነው?
06:50

Now Playing
መቆያ - ሙሀሙሽን የክፉ ልማድ ሰለባዎች - በእሸቴ አሰፋ
29:19
bottom of page

