top of page
የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።
መጋቢት 23/2018 የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ። ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አገልግሎቱ ተናግሯል። የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር ባደረገው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ካከማቹት በርካታ የኤሌክትሪክ ኬብልና ገመድ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋል ችለዋል ተብሏል። ኮተቤ ኪዳነ-ምህረት አካባቢ ተከማችተው የተገኙት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች 4 ሺ 895 ሜትር ኤቢሲና ዩጂ የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ 350 ኪ.ግ የሚመዝኑ የተለያዩ አልሙኒየምና መዳቦች ናቸው ተብሏል። አጠቃላይ የዋጋ ግምታቸውም 3 ሚሊየን 895 ሺህ 81
15 hours ago
ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ።
መጋቢት 23/2018 ሀገራዊ ምክክሩ የትግራይ ነገ የተረጋጋ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ የድርሻውን የሚወጣበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ። ለበርካታ ጊዜያት ሊከናወን ቀጠሮ ሲያዝ ሲራዘም የነበረው የትግራይ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። ከዛሬ መጋቢት 23 እስከ አርብ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ በሚካሄደው የመጀመሪያውን ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ከክልሉ የመጡና በአዲስ አበባ ያሉ የትግራይ ተወላጆች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ነው። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ትግራይ የሌለችበት ምክክር ግቡን የማይመታ በመሆኑ ከብዙ ጥረቶች በኋላ በአዲስ አበባ እንድ
15 hours ago


መጋቢት 22/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#ጀርመን በጀርመን ከሚኖሩ ስደተኞች 80 በመቶዎቹ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ተናገሩ፡፡ ሶሪያውያኑ ስደተኞች በመጪዎቹ 3 አመታት ከጀርመን ወደ አገራቸው ይሸኛሉ መባሉን ቢቢሲ ፅፏል፡፡ መራሄ መንግስት ሜርዝ 80 በመቶዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች በ3 አመታት ጊዜ ወደ አገራቸው እንደሚሸኙ እወቁልን ያሉት ከሶሪያው ጊዜያዊ ርዕሰ ብሔር አህመድ አልሻራ ጋር በበርሊን ከተነጋገሩ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ብዙዎቹ ሶሪያውያን ስደተኞች ጀርመን የገቡት በአገራቸው ተቀስቅሶ የነበረው ውስብስብ የእርስ በርስ ጦርነት በተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን ስደተኞቹን ከጀርመን መመለስ ይጀመራል ቢባልም ዝርዝሩ ገና አልታወቀም፡፡ ሶሪያ በአሁኑ ወቅት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረው በእጅጉ የተሻለ ፀጥታ እንደሚስተዋልባት መረጃው አስታውሷል፡፡ #አሜሪካ አ
1 day ago


ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡
መጋቢት 22/2018 ኢትዮጵያ በኢራኑ ጦርነት ምክንያት ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነዳጅ በላይ ገዝታ ማቅረብ ባለመቻሏ የነጭ ናፍጣ የቀን አቅርቦት በግማሽ ቀንሷል ተባለ፡፡ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የረዥም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል የነበራት ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ምርት ማቅረብ እንደማይችሉ ነግውኛል ብላለች፡፡ በመሆኑም ያለውን እጥረት መሰረት በማድረግ ከማዲያዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሰባት አካላት ተለይተው በመንግስት ይፋ ተደርገዋል፡፡ በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችለውን ውሳኔ ዛሬ ይፋ ያደረገው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡ ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ በየቀኑ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት 9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለታቸው ተሰ
2 days ago


ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡
መጋቢት 22/2018 ለትርፍ የተቋቋሙ የመንግስት ተቋማት ጭምር በበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰማርተው ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ እንደ ባንኮች፣ አምራች እንዱስትሪዎችና ሌሎችም የመንግስትና የግል አትራፊ ተቋማት በጎ አድራጎት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል። የተቋማቱ አትራፊነትና ስኬት ምንጭ ህዝብ እንደመሆኑ፣ አቅመ ደካሞችን በመርዳት ፣ ጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት፣ ወላጅ አልባ ህፃናትን በማስተማርና በሌሎችም በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ የማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የተጠየቀው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር "የፍቅር ሳምንት" የተሰኘ ዓመታዊ መርሃ ግብሩን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። #ሙዳይ_በጎ_አድራጎት_ማህበር ህፃናት፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ከልመና፣ ከጎዳና ተዳዳሪነትና
2 days ago


በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡
መጋቢት 22/2018 በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በኢትዮጵያ በዋጋ ግሽበት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ተናገረ፡፡ የኢራኑ ጦርነት በአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥም እየፈጠረ መሆኑን ኮሚቴው ማስታወሱን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡ ይህም በሃገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ጠቅሶ የስጋቱ ጫና ግን መንግስት በሚወስደው የመቆጣጠሪያ እርምጃዎች እና ግጭቱ በሚቆይበት ጊዜ የሚወሰን ይሆናል ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊስ ኮሚቴው ስድስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሄዶ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በመገምገም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በቅርቡ ሁለት ገለልተኛና የመስኩ ባለሙያ የሆኑ አባላትን ያካተተው የገንዘብ ፖሊሲ ከታህሳስ ወር
2 days ago


ታሪክን የኋሊት -የማይጨው ጦርነት
#ታሪክን_የኋሊት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የማይጨው ጦርነት የተደረገው በ1928 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ ኢጣሊያ በሊቢያና በሱማሊያ ከኢትዮጵያ ክፍል ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛ ከቆየች በኋላ፣ ጠቅላላ ኢትዮጵያን በሃይል ለመውረር ጦርነት ከፈተች፡፡ በምፅዋ ወደብ ፣ በኤርትራ በኩል ወደወሰን ዘመናዊ የጦር ሃይሏን አደራጀች፡፡ የወልወልን ግጭት ሆን ብላ ከቀሰቀሰች በኋላ፣ ተበዳይ ሆና ለመቅረብ ሞከረች፡፡ አከታትላም ዋናው የጦር ሃይሏን ባደራጀችባት ኤርትራ በኩል፣ ወሰን ጥሳ፣ በጥቅምት ወር መቀሌን ያዘች፡፡ ከወራሪው የኢጣሊያ ሃይል ጋር ሲወዳዳር፣ ኋላ ቀርና አነስተኛ መሣሪያ ያለው አብዛኛው፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የክተት አዋጁን ተከትሎ፣ ስንቁን ይዞ፣ ጦርና ጋሻውን አንግቦ ወደዘመቻው ተሰማራ፡፡ ኢጣሊያ፣ በሶማሊያ በኩል ባደራጀችው ዘመናዊ የ
2 days ago


በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ።
መጋቢት 22/2018 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሪል ስቴት ኤክስፖ በለንደን እንግሊዝ ከግንቦት 15 እስከ 17/2018 እንደሚካሄድ ተነገረ። በእንግሊዝና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው የመኖሪያ ቤት ማፍራት የሚችሉበትን ዕድል ለመፍጠር የተዘጋጀ ኤክስፖ ነው ተብሏል። በሪል ስቴት አልሚዎችና በተጠቃሚዎች መካከል ያለውን መተማመን ለማሳደግና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ግብይቶች እንዲፈፅሙ የተዘጋጁ ስርዓቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል። በኤክስፖው ላይ ከሚመለከታቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በሚደረግ የመረጃ ልውውጥና የፓናል ውይይት በዘርፉ ስላሉ ችግሮች ይነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም ኤክስፖውን አስመልክቶ ከተዘጋጀ መግለጫ ላይ ተመልክተናል። ባንኮች በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቢዝነስ ድ
2 days ago
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
3 days ago



Facebook
Twitter
Pinterest
Tumblr
Copy Link
Link Copied
Search video...

Now Playing
እስራኤል እና አሜሪካ ጦርነት አቁመው ከኢራን ጋር የስምምነት ፊርማ የሚያኖሩት መቼ ይሆን #Mamuasha #ማሟሻ
10:52

Now Playing
በአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኞች ለአደጋ ቅነሳ በሚል ከደመወዛቸው የመቆረጡ ጉዳይ
05:21

Now Playing
አየርላንድ ኢምባሲ ሴንት ፓትሪክ ቀንን በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪዎች ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ጋር በመሆን ያካሄዱት ዝግጅት Saint Patrick’s Day!
48:15

Now Playing
ለአእምሮ ጤና እክል አጋላጭ የሆኑ የስራ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው፣ምን ጥንቃቄ ማድረግስ ይገባል?
05:40

Now Playing
አልሰማንም እንዳትሉ - እናት ማናት?
05:56

Now Playing
መቆያ - ሞትን የናቀው ጦረኛ - ድራር አልዘዋር - በእሸቴ አሰፋ #shegerfm #mekoya
24:28

Now Playing
መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወልደማርያም እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ጋር የተደረገ ወግ መጋቢት 13/ 2018
40:57

Now Playing
ትዝታ ዘአራዳ - የጣሊያን ዘር ከሀበሻ ዘር እንዳይደባለቅ ይደነግግ የነበረው አዋጅ
20:46
bottom of page

