top of page


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡
መጋቢት 21/2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች #አሜሪካ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአገራቸው ጦር የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት መናኸሪያ የሆነውን የካርግ ደሴት ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ፡፡ የካርግ ደሴት የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ለውጭ ገበያ ከታለመው ነዳጅ 90 በመቶው የሚላከው ከዚሁ ደሴት እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ከወር በላይ ባስቆጠረው የኢራን ጦርነት ምክንያት በአለም ዙሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በጣሙን እያሻቀበ ነው ተብሏል፡፡ ኢራን በኢስፍሐን ዩኒቨርስቲ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት በእስራኤል እና በባሕረ ሰላጤው አገሮች በሚገኙ የአሜሪካ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የአፀፋ ጥቃት እንደምታደርስ ዝታለች፡፡ ኢራን በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል የኢንዱስትሪዎች መገኛ ላይ በፈፀመችው የሚሳየል ድብደባ ከባድ ቃጠሎ መድረሱ ታውቋል፡፡
Mar 302 min read


ጥቅምት 10 2018 - የውጪ ሀገራት ወሬዎች
#እስራኤል እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ዳግም የአየር ድብደባዋን ፈፀመች ተባለ፡፡ የእስራኤል ጦር ዳግም የአየር ድብደባውን የቀጠለው በጋዛ ደቡባዊ ክፍል እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡ ለደቡባዊ ጋዛው የአየር ድብደባ እስራኤል በሐማስ ትንኮሳ ተፈፅሞብኛ የሚል ክስ ማቅረቧን ተሰምቷል፡፡ የእስራኤል ጦር በሐማስ ፀረ ታንክ ሚሳየል ተተኩሶብኛ ብሏል፡፡ የፍልስጤማውያኑ ታጣቂ ቡድን ሐማስ በፊናው አንዲትም ጥይት አልተኮስኩም ማለቱ ተሰምቷል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለጋዛ ሰላም ባቀረቡት ባለ 20 ነጥቦች የሰላም እቅድ ተፋላሚዎቹ በተኩስ አቁም ሰንብተዋል፡፡ ይሁንና እስራኤል እና ሐማስ በተኩስ አቁም መጣስ መካሰሳቸው ተደጋግሟል፡፡ የእስራኤል ጦር ከትናንቱ የጋዛ የአየር ድብደባ በኋላ ወደ ተኩስ አቁሙ ተመልሻለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡ #ኬንያ የኬንያ የቀድሞ
Oct 20, 20252 min read
ፕሮግራሞች
bottom of page

