ጳጉሜ 3 2017 - ጄአር ፔትሮሊየም የተባለ ሀገር በቀል ኩባንያ የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ (ዲፖ) ሰርቶ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ
- sheger1021fm
- Sep 8, 2025
- 1 min read
ጄአር (JR) ፔትሮሊየም የተባለ ሀገር በቀል ኩባንያ የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ (ዲፖ) ሰርቶ ስራ ማስጀመሩን ተናገረ።
የነዳጅ ማከማቻ ዲፖውን ለመገንባት 2.5 ቢሊዬን ብር ወጪ እንደተደረገበትም ሰምተናል።
የጄአር ፔትሮሊየም ዋና ስራ አስኪያጅ ፀጋ ሀይሉ ዲፖው 9 ሚሊዬን ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ መያዝ ይችላል ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጇ "ጄአር ፔትሮልዬም ሰፈር ውስጥ ላምባ በመሸጥ ተጀምሮ ከቤት፣ ከተሸከርካሪዎች፣ ከማሽኖችና ከፋብሪካዎች እስከ አውሮፕላን ነዳጅ ማቅረብ ደረጃ የደረሰው ኩባንያ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ኩባንያው በአሁኑ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የሀይል ፍላጎት ለማሟላት ከ58 በላይ የነዳጅ ማደያዎችን በመገንባት እንዲሁም ከእህት ኩባንያው ''ደስታ ካሴ የግል ፈሳሽ ትራንስፖርት'' ጋር በመሆን ከ150 በላይ የነዳጅ ቦቴዎችን በማሰማራት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛልም ብለዋል፡፡
ጄአር (JR) ፔትሮሊየም የተሰኘው ሀገር በቀል ኩባንያ የተቋቋመው በ2009 ዓ/ም ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ ማከማቻ ዲፖ የተገነባውም በቦሌ ኤርፖርት አቅራቢያ እንደሆነም ሰምተናል።
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments