top of page

ጳጉሜ 3 2017 - የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ አንድ ዓመት በኋላ ታዲያ ኮንትሮባንድ በማስቀረት በኩል ምን አመጣ?

  • sheger1021fm
  • 11 minutes ago
  • 1 min read

በኢትዮጵያ የንግድ ሥርዓት ውስጥ የራስ ምታት ሆነው ከቀጠሉት መካከል ህገወጥ ንግድ ወይም ኮንትሮባንድ አንዱ ነው፡፡


ቡናና ጥራጥሬው፣ ማዕድኑ፣ በሬ፣ በጉ፣ ፍየሉ በየድንበሩ እየተነዱ፣ መድሃኒቱ፣ እፅ፣ አልበሳቱ ድንበር አሳብረው ወደ መሃል ሀገር እየገቡ ንግዱ ሲጎዱት ቆይተዋል፡፡


አሁንም ችግሩ አልተፈታም፡፡


ዘንድሮ እንኳን ግምታዊ ዋጋቸው 18.58 ቢሊዮን ብር የሆኑ እቃዎች በ #ኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ሲገቡ ተይዘዋል፡፡


2.81 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ እቃዎች ደግሞ ከሀገር ሲወጡ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡


በድምሩ 21.39 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በዚህ አመት ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡


ይሄ እንግዲህ መንግስት ደርሶበት በቁጥጥር ስር ያዋለው ነው፡፡


ይሄን የኮንትሮባንድ ጉዳይ መልክ ያስይዛሉ ከተባሉ ጉዳዮች መካከል አንደኛውና ዋነኛው አምና የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ይጠቀሳል፡፡


ያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ አንድ ዓመት በኋላ ታዲያ ኮንትሮባንድ በማስቀረት በኩል ምን አመጣ?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page