top of page

ጳጉሜ 3 2017 - ታክሲዎች ምሽት ላይ የሚያደርጉት ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪ አላስፈላጊ ወጪ እያስወጣቸው እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውናል

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች ምሽት ላይ የሚያደርጉት ህገወጥ የታሪፍ ጭማሪ አላስፈላጊ ወጪ እያስወጣቸው እንደሆነ ተጠቃሚዎች ነግረውናል፡፡


የስምሪት መስመሩን መደበኛ ታሪፍ በእጥፍ የሚያስከፍሉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዳሉም ሰምተናል፡፡


ያነጋገርናቸው የታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች በበኩላቸው እንዳንድ የስምሪት ተቆጣጣሪዎች ያለፍላጎታችን አምሽተን እድንሰራ ያስገድዱናል፤ ከመሸ ደግሞ ጭነን ስንሄድ እንጂ ስንመለስ ተሳፋሪ ስለማናገኝ የተወሰነ ጭማሪ እናደርጋለን ያም ቢሆን እንደሚባለው የተጋነነ አይደለም ብለውናል፡፡


ስለጉዳዩ የጠይቅናቸው በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ምሽት ላይ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች ያለ ስምሪት ገደብ ወደየሚገቡበት አካባቢ እየጫኑ እንዲሄዱ ስለፈቀድንላቸው ለታሪፍ ጭማሪው አሽከሪካሪዎቹ የሚያነሱት ምክንያት አሳማኝ አይደለም ይላሉ፡፡


ከተቀመጠለት የታሪፍ ክፍያ በተጨማሪ የጠየቃችሁ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ታርጋ በመያዝ 9417 ላይ በመደወል ጥቆማ መስጠት ትችላላችሁም ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ንጋት መኮንን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page