ጥቅምት 4 2018 - የቀድሞ ተዋጊዎች እና ሌሎች አካላት በትግራይ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ውስን በሆነ የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ውስጥ መግባታቸውን ጥናት አሳየ
- sheger1021fm
- Oct 14
- 1 min read
የቀድሞ ተዋጊዎች እና ሌሎች አካላት በትግራይ ክልል ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ውስን በሆነ የተፈጥሮ ሃብት ሽሚያ ውስጥ መግባታቸውን ጥናት አሳየ።
ሰላም፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ እድገት ተጋላጭ ለሆኑ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በሚል ሃሳብ የቀድሞውን መተማመን እና ችግር አፈታት ወደ ቀድሞው ለመመለስ ያለመ ጉባዔ ዛሬ እየተካሄደ ነው።
በጉባዔው ላይ ''በክልሉ መተማመን ለመፍጠር እና የቀድሞ ችግር አፈታትን መመለስ'' በሚል ርዕስ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ተጠንቶ ቀርቧል።
በጥናቱ መሰረት የሰሜኑ ጦርነት በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ሃብት መቀራመትን አባብሷል፣ የመንግስት መዋቅር ደካማ እንዲሆን እና ማህበራዊ ቀውስ የተባባሰ እንዲሆን አድርጓል ተብሏል።
የአካባቢ አስተዳደሮች ሙሰኞች ተደርገው በማህበረሰቡ እንዲሳሉ እና መንግስት እንዳይታመን የሰሜኑ ጦርነት ማድረጉን ጥናቱ ዘርዝሯል።
የቀድሞ ተዋጊዎች፣ አዳዲስ ተዋንያኖች፣ መደበኛ ያልሆኑ ቡድኖች ውስን በሆነው በክልሉ ሀብት ላይ ሽሚያ እንዲባባስ አድርጓል ተብሏል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ደግሞ የተቋማትን ታማኝነት ማረጋገጥ፣ ባህላዊውን የሰላም መንገድ መደገፍ፣ የተፈጥሮ ሃብትን መሰረት ያደረጉ ችግሮችን መፍታት እና አካታች የሆነ ንግግር ማድረግ ከችግሩ መውጫ ተደርገው ተቀምጠዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments