top of page

ጥቅምት 26፣2017 - የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ131 ሚሊዮን ብር ወጪ በቡና ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ድጋፍ አደረኩ አለ፡፡

  • Nov 5, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ131 ሚሊዮን ብር ወጪ በቡና ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ድጋፍ አደረኩ አለ፡፡


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ አደረኩ ያለው ከዩኤንዲፒ (UNDP) ባገኘሁት 9 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሏል፡፡


ከተገኘው ድጋፍ ላይም በመጀመሪያ ምዕራፍ 131 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለቡና ምርት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን መግዛቱን ተናግሯል፡፡


በዚህም በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልልን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎለታል፡፡


የቡናን ዘርፍ በመንግስት ከሚገኝ ገንዘብ ብቻ ማሳደግ እንደማይቻል የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) ከሌሎች ተቋማት ድጋፎችን በማፈላለግ ስራዎችን እየከወንን ነው ብለዋል፡፡


ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ተቋማት በተገኘ ድጋፍ ዘርፉን የማሳደግ ስራ ተሰርቷል የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤አሁንም ከ #UNDP የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለዘርፉ ማደግ ትልቅ አስተዋፆኦ አለው ብለዋል፡፡

የሚመረቱ ቡናዎች ጥራታቸው የተጠበቀ እንዲሆን እና ምርትን ለማሳደግ ይረዳሉ የተባሉ የተለያዩ ማሽኖች ለክልሎቹ ተሰጥቷል፡፡


ያረጁ የቡና ዝርያዎችን በአዳዲስ መተካት እና መጎንደል የሚያስችሉ ማሽኖችን ግዥ ተከናውኖ ለአርሶ አደሮች መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡


ከ UNDP የተገኘው አጠቃላይ ድጋፍም 440,000 የሚሆኑ አነስተኛ የቡና አልሚዎች እንደሚደግፍ የተናገሩት በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ወርቁ ፕሮጀክቱ ከአራቱም ክልሎች 22 ወረዳዎችን ተደራሽ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከ UNDP ባገኘው ድጋፍ በአራቱም ክልል 22 ወረዳዎች ላይ ስራዎችን የሚሰራ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን የሰባት ዓመት እድሜ ያለው ፕሮጀክት ነው ተብሎለታል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ

Recent Posts

See All
የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡

ነሐሴ 7 2018 የኤሌክትሪክ ታሪፍ በየጊዜው ሲጨምር ይታያል፡፡ በዚህም ደንበኞች ቅሬታ ያቀርባሉ ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ አዲስ የታሪፍ ጭማሪ አለማድረጉን፤ የአሁኑ የዋጋ ለውጥ ከ2017 ጀምሮ በ16 ዙር ለማስፈጸም የታቀደው አሰራር አካል ነው ብሏል፡፡ እንደውም ከሁለት አመት በፊት ተግባራዊ ያ

 
 
 
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡

ነሐሴ 6 2018 ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page