top of page

ጥቅምት 20 2018በፋብሪካ የተቀነባበሩ እንዲሁም ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት የሚደርሱ የጤና ጉዳቶች ኢትዮጵያን ብዙ ወጪ እያስወጣት ነው ተባለ።

  • sheger1021fm
  • Oct 30
  • 1 min read


ሀገሪቱ በዚህ በየዓመቱ ከ31 ቢሊየን ብር በላይ ታወጣለች ተብሏል።


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተለወጠ የመጣው የአመጋገብ ሥርዓት ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ጫና ከ52 በመቶ በላይ እንዲሆን ማድረጉ ተነግሯል።


ይህንን ያስቀራል በሚል በዝግጅት ላይ ያለውን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጡ ምግቦችን የሚቆጣጠር ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ የማህበረሰብ ጤናን የሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰራው የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ህብረት እና ሌሎች የሲቪል ማህበራት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።


በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት በትብብር እየተሰናዳ ያለው ረቂቅ አዋጅ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ምክንያት የሚደርሱ የጤና እንዲሁም ሌሎች ጫናዎችን ለመቀነስ የሚያግዝና ይህንንም በተለያዩ መንገዶች እንደሚደግፋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ ከሌሎች ጊዜያት በተለየ እንደ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ኩላሊት መድከምና ካንሰር ያሉ ህመሞች በሀገሪቱ ከሚከሰቱ ሞቶች ከ52 በመቶ በላይ ለሚሆኑት  ምክንያት ነው ተብሏል።


ጤናማ ባልሆነ ምግብ ምክንያት የሚመጡት እነዚህ ተጽዕኗቸው ጤና ላይ ብቻ አለመሆኑ የተነገረ ሲሆን ኢትዮጵያ በሽታዎቹን ለመከላከል እንዲሁም ለህክምና  በየአመቱ 31.3 ቢሊዮን ብር እያስወጣት ነው ይህም ኢኮኖሚን ጭምር የሚጎዳ ነው በጊዜ መፍትሄ ካልተሰጠውም ጉዳቱ እየጨመረ የሚሄድ እንደሆነ ተነግሯል።


ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ምርትን የሚቆጣጠር አዋጅ ተግባራዊ በተደረገባቸው ሌሎች ሀገራት ከ6 እስከ 15 በመቶ ለውጥ መጥቷል የበሽታዎቹም ጫና ቀንሷል ተብሏል።


ረቂቅ አዋጁ የተሰናዳው ምርቶቹ ሙሉ በሙሉ እንዳይመረቱ ለማስቆም ሳይሆን የህብረተሰብን ጤና በማይጎዳ መልኩ እንዲመረቱና ተጠቃሚዎችም ሙሉ መረጃ ይዘውና አውቀው እንዲጠቀሙ ለማድረግ ነው ሲሉ የኮርሃ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበበ ከበደ ተናግረዋል።


አዋጁ ጸድቆ ብቻውን ስራ ላይ ቢውል ለውጥ የማያመጣ በመሆኑም የታክስ እንዲሁም የፖሊሲ ማሻሻያ እና ትምህርትና መረጃ መስጠት ይጠይቃል መባሉን ሰምተናል።


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page