ጥቅምት 20 2018"ሰላም በሌለበት ኢንስትመንትም ሆነ የስራ እድል መፍጠር አይቻልም" ሲሉ የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ተናገሩ።
- sheger1021fm
- Oct 30
- 1 min read
ፕሬዝዳንቷ ይህ የተናገሩት ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም "የንግድ ሚና ለሰላም ግንባታ'' በሚል ሃሳብ አዲስ አበባ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባሰናዳው የፓናል ወይይት ላይ ነው።
ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት ሆነ ለሌላ ስራ ሰላም መሰረት መሆኑን ያስረዱት ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ያለ ሰላም ንግድን ማሰብ ከባድ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የሰላም መስፍን ለሀገር ችግር መፍትሔ ነውም ብለዋል።
የሰላም እጦት ንግድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር፣ ምርት ከቦታ መንቀሳቀስ እንዳይችል ማድረጉን ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ ተናግረዋል።
ሰላም እንዲኖር ደግሞ የመግስት እና የግሉ ዘርፍ ምክክር አስፈላጊ ሲሉ ጠቁመዋል።
የስራ እድል ኢንዲፈጠር፣ ኢንቨስትመንትም ኢንዲበረታታ ደግሞ ሰላም መሰረት መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሃራ ሞሃመድ አስረድተዋል።
የሰላም እጦት የሰው ልጅን፣ ንግድ እና ለኢንቨስትመንት ብቻ ሳይሆን እንስሳት እና እጽዋትም ጭምር የሚጎዳ መሆኑን በአግባቡ መረዳት አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ጉባዔ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ናቸው።
ንግድ የሰው ልጆች የሚያግባባበት እና የሚረዳዳበት እንደሆነ ጠቅሰው ምክንያቱ ደግሞ ንግድ አገናኝ ስለሆነ ነው ብለዋል።
ሰው ሲገዛም ሆነ ሲሸጥ ተነጋግሮ፣ ተወያይቶ ነው ያሉት ቀሲስ ታጋይ ሰላም ከሌለ ግን እነዚህ ግንኙነቶች ይቀራሉ መነጋገርም ይቀራል ሲሉ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የሰላም እጦት በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ያስረዱት ፀሃፊው በዚህም ምክንያት ኢንዱስትሪዎች ሲወድሙ ንግድ ሲቋረጥ እያያን ነው ይህን ማስተካካል ያስፈልጋል ይህ ካልሆነ ግን በሌሎች ሰፈር ያየነውን እኛ ጋርም መምጣቱ አይቀሬ ነው ብለዋል።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ጉባዔ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ( ፕ/ር ) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments