top of page

ጥቅምት 11 2018 - የጫኝ እና አውራጅ ጉዳይ

  • sheger1021fm
  • 1 hour ago
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ከተማ አንዱ የነዋሪዎች ፈተና የጫኝ እና አውራጅ ጉዳይ ነው፡፡


አንድ ሰው ቤት ለመቀየር ፈልጎ እቃውን ሲያጓጉዝ ጫኝ እና አውራጆቹ እቃውን የምንጭነውም ይሁን የምናወርደው እራሳችን በምንተምነው ገንዘብ ነው እያሉ ነዋሪውን ሲያስመርሩት መመልከት የተለመደ ጉዳይ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡


ይህ ደግሞ ነዋሪዎችን ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተደማምሮ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡


ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየአካባቢው በህጋዊ መንገድ የተሰማሩ ጫኝ እና አውራጅን በዘመናዊ መልኩ የሚሰሩ ተቋማት በርከትከት እያሉ ነው፡፡


ከእነዚያም መካከል አንዱ መላ ሎጅስቲክስ ሰርቪስ ነው፡፡


መላ ሎጅስቲክስ ሰርቪስ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ የሆነው የቤት ቅየራ አገልግሎት ወደ ስራ ከገባ የአንድ ዓመት እድሜ እንደያዘ የተነገረ ሲሆን የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን፣ ቢሮዎችን እና መጋዘኖችን የመቀየር አገልግሎት እየሰጠን ነው ተብሏል።


ለመሆኑ አሁን እየተለመደ የመጣው ይህ አሰራር ወጪን ከመቀነስ አኳያ የነዋሪውን እንግልትም ከመቀነስ ጋር ተያይዞ ምን ምን እየሰራ ነው? ምን ዓይነት አገልግሎቶችንስ ነው እየሰጠ ያለው?


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page