ጥቅምት 1 2018 ዘመን ባንክ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ መሆኑን ተናገረ።
- sheger1021fm
- Oct 11, 2025
- 1 min read
የአንድ አክሲዮን ትርፍ ወደ 68.3 በመቶ ማደጉንም አስረድቷል።
ዘመን ባንክ በ2017 በጀት ዓመት 14.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን በዛሬው እለት ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ባወጣው ሪፖርት ተናግሯል።
የባንኩ የተጣራ ትርፉም 5.87 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህም ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ145 በመቶ ጨምሯል ተብሏል፡፡
የባንኩ አጠቃላይ ሀብት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 88.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል ይህም ካለፈው ዓመት በ49.7 በመቶ ጭማሪን ያሳየ መሆኑ በሪፖቱ ተጠቅሷል።

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 13.2 ቢሊዮን ብር ፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 9.4 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተሰምቷል።
የባንኩ የተበላሸ የብድር መጠን 2.81 በመቶ ብቻ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ5 በመቶ አኳያ ሲታይ ጤናማ መሆኑን ያሳያል ተብሏል።
በዘመን ባንክ በሂሳብ አመቱ የተንቀሳቀሰው የውጭ ምንዛሪ ፍስት 588 ሚሊዮን ዶላር ነው፣ ይህም ባንኩ የንግድ ልውውጥ እና ዓለም አቀፍ ንግድን በማመቻቸት ረገድ ቀዳሚ አጋር መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን ያሳል ተብሏል።
ከመተሰረተ 17 ዓመት የሆነው ዘመን ባንክ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ 132 ቅርንጫፎች አሉኝ ብሏል፡፡
ዘመን ባንክ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 61.86 ሚሊዮን ብር መስጠቱን በሪፖርቱ ጠቅሷል።
የዘመን ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር ባንኩ ዛሬ ባደረገው ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር "ወደ ካፒታል ገበያ፤ ኢንቨስትመንት ባንኪንግ እና ሌሎች ስትራቴጂያዊ ተግባራት ለመግባት ወሳኝ መሠረት እየጣልን ነው"ብለዋል፡፡
የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚአቶ ደረጀ ዘበነ በበኩላቸው “ባንኩ ያመጣቸው ስኬቶች ጠንካራ የአስተዳደር፣ በደንበኞች ላይ ያተኮረ የንግድ ፍልስፍናና የሠራተኞቻችን ቁርጠኛነት ምስክሮች ናቸው" ሲሉ ስረድተዋል፡፡
ንጋቱ ሙለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp ፡ https://tinyurl.com/ycxjmm3s
👔LinkedIn ፡ https://tinyurl.com/tyfaekvx












Comments