top of page

ጥር 22፣ 2015- ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ ዳግም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሊቀጥሉ ነው ተባለ


ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ ዳግም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሊቀጥሉ ነው ተባለ፡፡


የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቀጠያው ንግግር በቅርቡ እንደሚከናወን የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያን መናገራቸውን ቻይና ኦርግ ድረ ገፅ ፅፏል፡፡


የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ከኩዌት ጋርም ግንኙነታችን በእጅጉ እየተሻሻለ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ በኢራቅ አመቻችነት የግንኙነት ማሻሻያ ንግግር ሲያደርጉ መቆየታቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡


ዲፕማሲያዊ ግንኙነታቸው ከተቋረጠ 7 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡


ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ በሃይማኖታዊ ዘውግ እና በአካባቢያ ተፅዕኖ አሳዳሪነት ተቀናቃኝነታቸው የጎላ መሆኑ ይነገራል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


bottom of page