top of page

ጥር 20 2017 - የሸማቾችን መብት እንዲያስጠብቅ የተቋቋመው ተቋም ከሸማቹ በቂ ቅሬታ እየቀረበልኝ አይደለም አለ

  • sheger1021fm
  • Jan 28
  • 2 min read

ከንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣንነት በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስር ወዳለ ዴስክ ዝቅ ያለውና የሸማቾችን መብት እንዲያስጠብቅ የተቋቋመው ተቋም ከሸማቹ በቂ ቅሬታ እየቀረበልኝ አይደለም አለ፡፡


የሸማቹን መብት ያስጠብቃል፣ በነጋዴዎች መካከል ያለው የንግድ ውድድር ህግን የተከተለ እንዲሆን ይሰራል ተብሎ በባለስልጣን ደረጃ በአዋጅ ተቋቁሞ የነበረው ተቋም፣ ፈርሶ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ስር በዳሬክቶሬት ደረጃ ይገኛል፡፡


ተቋሙ ምንም እንኳን ስራው በዚህ የተገደበ ቢሆንም በግብይት ወቅት ሸማቹ ተበደልኩ ብሎ ለሚያቀርበው ቅሬታ ምላሽ እየሰጠ መሆኑን ነግሮናል፡፡


በተለይ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ስር ያለው የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳሬክቶሬት ሸማቹ የሚያቀርብልኝ የመበት ጥሰጥ ቅሬታ ካለው ችግር አንጻር በቂ አይደለም፣ የመንፈቅ ዓመቱን እንኳን ብንመለከት የቀረቡት155 ቅሬታዎች ብቻ መሆነናቸውን ነግሮናል፡፡


ይህም የመጣው አንድም ሸማቹ በግብይት ወቅት ያለውን መብት ባለማወቁ፤ ከዚህም ባሻገር ችግሩን የሚፈታለት ተቋም ስለመኖሩም ባለማወቁ ነው ብሏል፡፡

ree

ከሚቀርቡት ቅሬታዎች የሚበዙት የጥራት ጉድለት ተሽጦልኛል የሚሉ ናቸው የሚሉት የሸማቾች መብት ጥበቃ ዳሬክተር አቶ ሰፋለም አቦረዳኝ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ባለሙያ መድበን የተባለው ችግር መኖሩን በማጣራት ነጋዴዉንና ሸማቹን በማደራደር ሸማቹ እቃውን መልሶ ገንዘቡ እንዲመልስለት እናደርጋለን ብለዋል፡፡


በሸማቾች መብትና ጥበቃ አዋጅ ላይ በተቀመጠው መሰረት አንድ ሸማች ጥራት የጎደለው ምርት የተሸጠለት እንደሆነ በ16 ቀን ውስጥ እቃው በነበረበት አኳኋን መመለስ እንደሚችል አስቀምጧል ሲሉም አስረድተዋል፡፡


ምንም እንኳን የሸማቹን መብት ለመጠበቅ እየሰራን ቢሆንም በንግድ እንቅስቃሴው ያለውን የማጭበርበርና ማንኛውም የሸማቹን የመብት ጥሰት እግር በእግር እተከተልን እየፈታን ነው ማለት አንችልም የሚሉት አቶ ሰፋለም፣ ለሚቀርብልን ማንኛውም ቅሬታ በድርድር ከመፍታት በፍርድ ቤት ቆሞ እስከ መከራከር የሚደርስ ሃላፊነት እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡


ከሚቀርቡት የተጭበርብሪለሁ ቅሬታ የሚበዙት በድርድር የሚፈቱ ናቸው በዚህ መንገድ ችግሩ ካልተፈታ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት እንወስደዋለንም፤ ይህ ዓመት ከተጀመረ ወደ ፍርድ ቤት የወሰድነው የለም ብለውናል፡፡


በየትኛው ጊዜ በግብይት ወቅት ለሚገጥማችሁ ችግርም ይሁን ቅሬታ በከተማዋ ንግድ ቢሮ የጥቆማ መስጫ በ8588 መስመር እንዲሁም በአካል በመቅረብ ቅሬታው ቢቀርብልን ባለሙያዎች መድበን የሸማቹን መብት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡


የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ንግድ በህግና ስርዓት እየተመራ ባለመሆኑ ሸማቹ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል፤ ሸማቹን ይጠብቃል ተብሎ ተቋቁሞ  የነበረው ከንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ወደ ነበረበት መመለስ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡


ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page