top of page

ጥር  2፣2016 - የፖለቲካ ፓርቲዎች  የጋራ ምክር ቤት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመውን ስምምነት ያለ ልዩነት እቀበለዋለው አለ

 ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመውን ስምምነት ያለ ልዩነት እቀበለዋለው ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች  የጋራ ምክር ቤት ተናገረ።

 

የጋራ ምክር ቤቱ ትናንት ጥር 01፣ ቀን 2016 ዓ.ም ያደረገውን ጠቅላላ ጉባዔ ተከትሎ መግለጫ አውጥቷል።

 

በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን "መግባቢያ ሰነድ" በተመለከተ የስምምነቱን ማዕቀፍ፣ ዝርዝር ይዘቱን እና ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ባሉት እድሎችና ስጋቶች ላይ በዝርዝር መወያየታቸውን አብራርቷል።

 

ስምምነቱም ያለልዩነት እንደግፈዋለን ያለው መግለጫው መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህብረተሰብም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

 

አካታች ሀገራዊ ምክክርን በተመለከተ የጋራ ምክር ቤቱ መወያየቱም ተሰምቷል።

 

ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ  በቀረበው ሪፓርትና ማብራሪያ ላይ ውይይት ማድረጉን የገለፀው የጋራ ምክር ቤቱ ለምክክሩ ውጤታማነት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ከውሳኔ መድረሱን ይፋ አድርጓል።

 

በምክክር ሂደቱ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሳተፉም ጥሪውን አቅርቧል።

 

ለምክክር ኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬት እንቅፋት እየሆነ ያለውን የሰላምና የጸጥታ ችግር በመቅረፍ በኩልም መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህዝብ የበኩሉን ሊያደርግ ይገባልም ብሏል መግለጫው።

 





የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

 

 

 

bottom of page