ግንቦት 7 2017 - የፍቺ ቁጥርን ለመቀነስ የቅድመ የጋብቻ ስልጠና እየሰጠሁ ነው ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- May 15
- 1 min read
የፍቺ ቁጥርን ለመቀነስ የቅድመ የጋብቻ ስልጠና እየሰጠሁ ነው ሲል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ይህ የተባለው ዛሬ ለሚከበረው የቤተሰብ ቀንን አስመልክቶ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡
በዚህም ሰዎች ለፍቺ ከመዳረጋቸው አስቀድሞ ወደ ትዳርም ከመግባታቸው በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱና የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ከተቋሙ ሰምተናል፡፡
ይህም ወደ ትዳር ከገቡ በኋላ የሚገጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡
ስልጠናው የሚሰጠው ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ወደ ትዳር ከገቡ በኋላና በትዳር ላይ ሆነው የሚወስዱት እንደሆነ የተናገሩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ሁርያ አሊ ናቸው፡፡
ከቤተሰብ አካላት መካከል የሆኑት ህፃናት ሴቶች የአካል ጉዳተኞች እንዲሁም አዛውንቶች የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሆነ ሚኒስትር ድኤታዋ ተናግረዋል፡፡
በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት ችግር ለሚደርስባቸው ሰዎችም ከተለያዩ ረጅ ተቋማት ጋር በመሆን ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነም ሰምተናል፡፡
ይሁንና ድጋፉ የሚገባቸው እያሉ ያልተገባቸው ይወስዱ እንደነበር እና ይህንን ለማስተካከል የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋቱንም አስረድተዋል፡፡
የቤተሰብ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ32ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ‘’የተሻሻለ የቤተሰብ ገቢ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ’’ በሚል ለ3ተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 7 2017 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ












Comments