ግንቦት 6 2017 - የፈንታሌ የመስኖ ፕሮጀክት 18,000 ሄክታር መሬት እንዲያለማ ሆኖ ቢገነባም እያለማ ያለው ከ6,000 ሄክታር እንደማይበልጥ ጥናት አሳየ፡፡
- sheger1021fm
- 41 minutes ago
- 1 min read
የፈንታሌ የመስኖ ፕሮጀክት 18,000 ሄክታር መሬት እንዲያለማ ሆኖ ቢገነባም እያለማ ያለው ከ6,000 ሄክታር እንደማይበልጥ ጥናት አሳየ፡፡
የአካባቢውን አርብቶ አደር ወደ ከፊል አርብቶ አደርነት ያሸነግራል ተብሎ የተገነባው ይኸው ግድብ የታለመለትን ዓላማ እንዳላሳካ ጥናት አሳይቷል፡፡
ከግድቡ የሚባክነው ውሃም በአካባቢው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ ነው ተብሏል፡፡
ጥናቱ ምን አሳየ፤
- ከአዋሽ ተጠልፎ ወደ ግድቡ ከሚገባው ውሃ 12 ሺህ ሄክታር የሚያለማው ውሃ እየባከነ ነው፡፡
- የሚባክነው ውሃ ጨዋማ በመሆኑ አካባቢውን አፈር ጨዋማነት ያባብሳል፡፡
- የከርሰ ምድር ውሃው ከፋ እንዲል በማድረግ ምርታማነት እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
በመሆኑም ያልተጠናቀቁት የመስኖ ፕሮጀክቶች እንዲያልቁ ተጠይቋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN