top of page

ግንቦት 5 2017 - የአሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ደንበኞቼ በ"ኮፔይ ኢ-ብር" መተግበሪያ አማካኝነት የተጠቀሙበትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት መክፈል ይችላሉ ሲል ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • 21 hours ago
  • 1 min read

ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው እና የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው ተፈራርመዋል ።


የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ ከ17 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች በ"ኮፔይ ኢ-ብር "የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት የኤሌክትሪክ ክፍያቸውን ከዛሬ ጀምሮ መፈፀም ይችላሉ ብሏል።

የባንኩ ደንበኞች ያልሆኑ ሰዎችም ባንኩ ባሉት 35 ሺህ በላይ ወኪሎች ጋር ሄደው ክፍያቸውን መፈፀም ይችላሉ ሲባል ሰምተናል።


ክፍያውን በUSDD 841 ላይ መክል እንደሚቻል ተነግሯል ።


የኦሮሚያ ኅብረት ባንክ ኮፔይ ኢ-ብር አስካሁን ድረስ ከ3 ትሪሊዮን ብር በላይ እንደተገላበጠበት ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።


የዛሬው የክፍያ ሥርዓት ስምምነት ደንበኞች ያለ ውጣ ውረድ በጊዜና ቦታ ሳይገደቡ ካሉበት፥ የሥራ ቀን፣ ሰንበትና የበዓላት ቀን ሳይል በፈለጉት ጊዜ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍያቸውን መፈጸም የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።


የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንከ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደርቤ አስፋው በኮፔይ ኢ-ብር የኤሌክትሪክ ከፍያን ለመፈጸም በዛሬው ቀን የተጀመረው ዲጂታል አገልግሎት የማህበረሰቡን አኗኗር የመለወጥ ዓላማውን ዕውን በማድረግ ድርሻ እንደሚኖረው ተናግረዋል ።


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካሉት 5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞቹ 90 በመቶዎቹ በዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን እንደሚፈፅሙ ስራ አስፈፃሚው ጌቱ ገረመው አስረድተዋል።


እስካሁን ድረስ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች በቴሌ ብር ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ክፍያዎችን ሲከፍሉ መቆየታቸው ያስታወሱት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚው ጌቱ ገረመው የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ ወደዚህ መግባቱ የክፍያ አሰባሰቡን ቀላል እንደሚያደርግላቸው አስረድተዋል።


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page