top of page

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፉት 10 አመታት ሲሰጥ የቆየው ከወለድ ነፃ "ንብ ሃላል" የባንክ አገልግሎት ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ነው አለ።

  • 6 hours ago
  • 1 min read

ሰኔ 22/2018


ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለፉት 10 አመታት ሲሰጥ የቆየው ከወለድ ነፃ "ንብ ሃላል" የባንክ አገልግሎት ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ነው አለ።



ለዚህም የ10 አመታት ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደንበኞቹ እና ሰራተኞቹ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።


ይህ ማለት ግን የተሰራው ስራ በቂ ነው ማለት አይደለም ያለው ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን በተመለከተ ካለው የደንበኞች ፍላጎት አንፃር ከዚህ በላይ መስራት እንዳለብን ይጠቁመናል ብሏል።


ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ይህንን ያለው ባለፉት 10 አመታት "ንብ ሃላል" ከወልድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 10ኛ አመት ክብረ በዓል ማጠቃለያ መርሃ - ግብር ባካሄድበት ወቅት ነው።


ባንኩ "ንብ ሃላል" ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 10ኛ አመግ ክብረ-በዓል ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ ሁነቶች ሲያከብር መቆየቱን የተናገረ ሲሆን የማጠቃለያ ዝግጅቱን ዛሬ አካሂዷል።


በማጠቃለያ መርሀ-ግብሩ በተደረገው የንብ ሀላል የ10 አመታት ጉዞ ሂደት አገልግሎቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች፣ የደንበኞች ቁጥር እና የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ዕድገት በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።


በቴክኖሎጂ የተደገፉ አዳዲስ የቁጠባ ሂሳቦችንና በዲጅታል አማራጮች የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር ወደፊት አገልግሎቱን አዘምኖ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ያነሳው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገና የሸሪዓ መርሆችን የጠበቁ አገልግሎቶችን አጠናክሮ ለመስጠን ማቀዱን ተናግሯል።


ባንኩ የ"ንብ ሃላል" አገልግሎቱን በሁሉም መደበኛ እና ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎቹ አማካይነት ለደንበኞች ተደራሽ እንዲሆን እያደረኩ ነው ያለ ሲሆን ታህሳስ 8 ቀን 2008 ዓ.ም የጀመረውን የንብ ሀላል አገልግሎት መለያ በአዲስ መልክ አዘጋጅቻለሁ በቅርቡም ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ



Recent Posts

See All
ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡

ሰኔ 22/2018 ዘንድሮ በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 66 በመቶዎቹ ተማሪዎቻቸው ሙሉ በሙሉ የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ በሰጠው መግለጫ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች 95 ነጥብ 8 በመቶ፤ ከግል ት/ቤት ተማሪዎች ደግሞ ከ99

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page