ግንቦት 22 2017 - የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች እና አከፋፋይ ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር አብሬ መስራት ጀመርኩ አለ።
- sheger1021fm
- May 30
- 1 min read
የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች እና አከፋፋይ ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር አብሬ መስራት ጀመርኩ አለ።
ዶዳይ የሐገሪቱን የኤሌትሪክ ትራንስፖርት አጀንዳ ለመደገፍ ባለኝ ቁርጠኝነት 40 የኤሌክትሪክ ሞተሮች ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሰጥቻለሁ ብሏል።
የተበረከቱት ኤሌክትሪክ -ሞተር ሳይክሎች ከዶዳይ ዘመናዊ የባትሪ መለዋወጫ አውታር ጋር ሙሉ ለሙሉ የተገናኙ ሲሆኑ ከዶዳይ ስማርት ኔትወርክ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው፤ አሸክርካሪዎች በስልካቸው ክፍያ እንዲከፍሉ እና ሃይል ያለቀበትን ባትሪያቸውን በ5 ደቂቃ ወዲያውኑ ሙሉ በሙሉ ቻርጅ ባረገ ባትሪ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል ተብሏል ።

ኩባንያው ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር ያደረገው ስትራቴጂካዊ ትስስር የከተማ ትራንስፖርትን ለማሳደግ፣ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ዘላቂነት ለማስተዋወቅ እና ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች አዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው መሆኑ ተጠቅሷል።
የዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዩማ ሳሳኪ " ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከወሳኝ የከተማ ተቋማት ጋር በመተባበር ስራ በመጀመራችን ደስታ ይሰማናል" ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል ።
የጃፓኑ ዶዳይ ኩባንያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራችና አከፋፋይ ሲሆን አዳዲስ እና ዘላቂ የትራንስፖርት መፍትሄዎችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነኝ ብሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Comments