top of page

ግንቦት 20 2017 -ንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኝ ኢትዮጵያዊያን ከ40 በመቶ አይበልጡም፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 days ago
  • 1 min read

ንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኝ ኢትዮጵያዊያን ከ40 በመቶ አይበልጡም፡፡


በገጠር ደግሞ እስከ 70 በመቶው የንጹህ መጠጥ ውሃ ማግኘት አልቻለም፡፡


እንደ ጎንድር፣ ሻሸመኔ፣ ጌዲዮ እና ሰሜን ወሎን ጨምሮ መሰረታዊ የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር ያለባቸው የሀገሪቱ ከተሞች እና አካባቢዎች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተጠይቋል፡፡


ታሪካዊ እና ጥንታዊ የሆነችው ጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋኗ 21 በመቶ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


በኢትዮጵያ ውሃ ዳር የሚኖሩ አካባቢዎች ጭምር ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዳለባቸው የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡


የምክር ቤት አባላቱ ይህን የተናገሩት እና ችግሩ እንዲፈታ የጠየቁት በትናንትናው እለት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከምክር ቤት አባላት ለተነሱለት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በፓርላማ በተሰየመበት ወቅት ነው፡፡


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበኩሉ የመጠት ውሃ ሽፋንን ላማሳደግ እየሰራ እንዳለ ተናግሮ መስኩ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚጠይቅ ሁሉም ድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…….




ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page